+251118132191
contact@mint.gov.et
ሚኒስትሮቹ የገላን ጉራ የተቀናጀ መንደርን እና ሌሎች የልማት እንቅስቃሴወችን ጎበኙ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር ከፍተኛ አመራሮች 5ኛ ቀኑን በያዘው የአዲስ አበባ ከተማ የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራዎች በዛሬው እለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተሰሩ በርካታ የልማት ስራዎችን ከስራ ሀላፊዎች ጋር ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
ሱፐርቪዥኑ በየክፍለ ከተማው ያሉ ስራዎች ላይ ቅኝት በማድረግ፤ ጥሩ ስራወችን በማበረታታትና ክፍተቶች ላይ የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለተሻለ ውጤት መትጋት ነው።
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በአዲስ አበባ ከተማ በተፈጠሩ ምቹ የልማት ሁኔታዎችን ስናይ የሚያስደስት ስሜት በውስጣችን እዲፈጠር አድርጓል ብለዋል።
ሀገራችን የዲጂታል ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የተቀናጀ የልማት ስራዎችን በማዘመን የምንፈልገውን የኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት ማምጣት እንደሚቻል ብዙ በሞዴልነት የሚጠቀሱ ስራዎችን ማየት መቻላቸውን ገልፀዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እኛ በምናውቃቸው ልክ ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው የሚያስችሉ ስራዎች መሰራት አለባቸው ብለዋል።
በአጭር ጊዜ የተሰሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ከቻልን በአጭር ጊዜ እልፍ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚቻል አንስተዋል።
ተጠናክሮ የቀጠለው የመስክ ምልከታ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች የመኖሪያ አካባቢ የገላን ጉራ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር፣ የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ፣ የአቅመ ደካሞች ምገባ፣ የተቀናጀ የከተማ እንሰሳት ግብርና እና የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ የስፖርት ማዘውተሪያወች እና መሠል ስራወች ያሉበትን የተመለከተ ሲሆን በቀጣይ ቀናት የሱፐርቪዥን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች