+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ሰባተኛው የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ዓመታዊ የምርምር ግምገማ ተካሄደ!

የባዮ እና ኢመርንጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዓመታዊ በኢንስቲትዩቱ በሚካሄዱት የምርምር ፕሮጀክቶች ላይ ግምገማ አካሂደዋል።

በምርምር ግምገማው በባዮቴክኖሎጂ እና በኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ማዕከል ስር በሚካሄዱ አዳዲስ ፣ከዚህ ቀደም የተጀመሩና ፤ የተጠናቀቁ የምርምር ስራ ውጤቶች ተገምግመዋል ።

በዚህም መሰረት 60 የሚሆኑ አዳዲስ ችግር ፈች የምርምር ንድፈ-ሀሳቦች ቀርበው የተገመገሙ ሲሆን 86 በሂደት ላይ የነበሩ ፕሮጀክቶች እንዲሁም 7 የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎች ቀርበው ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል ።

ለአንድ ሳምንት የቆየው ይህ የኢንስቲትዩቱ የምርምር ግምገማ መረሀ-ግብር በሁለት ዘርፎች የ10 ዳይሬክተሮች የምርምር ስራዎችና ሀሳቦችን በመገምገም ከወትሮው የተለየ አዳዲስና ጠንካራ ችግር ፈች፣ ሀብት አመንጭና ስራ ፈጣሪ እንዲሁም ባዮ-ኢኮኖሚ ተኮር የምርምር ሀሳቦች ቀርበውበት ተመራማሪዎችን ያነቃቃና ተሳታፊነትን ከፍ ያደረገ መሆን ችሏል።

በሂደት ላይ ላሉ የምርምር ስራዎችም የሚጠናከሩበትና የሚጠናቀቁበት አቅጣጫ ላይ በምርምር ግምገማው ወቅት በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ እና በም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀይሉ ዳዲ አማካኝነት አቅጣጫ ተሰጥቶበታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ