+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ስልጠናው የተሻለ የቴክኖሎጂ ክህሎት እንድናገኝ አስችሎናል

የኢትዮጵያን ኮደርስ ዲጂታል ስልጠና በቴክኖሎጂው የተሻለ ክህሎት እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ በሐረሪ ክልል ስልጠናውን እየተከታተሉ የሚገኙ ወጣቶች ገለጹ።

በሐረሪ ክልል ከ 2ሺህ 600 በላይ ወጣቶች የኢትዮጵያን ኮደርስ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።

በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ የነበራቸውን ክህሎት በማዳበር የተሻለ ክህሎት እንዲያገኙ እያስቻላቸው መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይ ለወጣቱ እንደዚህ ዓይነት ስልጠናዎችን መስጠት አገሪቷ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያከናወነች የምትገኘውን ስራ በማገዝ ትልቅ አስተዋጽዎ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል።

ስልጠናው የራስን አቅም ከመገንባት ባለፈ ለአገር የሚጠቅም በመሆኑ ስልጠናው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የሐረሪ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም በሀገሪቱ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው፣ ስልጠናው ትውልዱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማነፅ አገሪቱ ያላትን የሰው ሀይል ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችላትን እድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልፀዋል።

በክልሉ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊው፣ በተለይ በክልል ደረጃ ዲጂታል ሐረሪን ከመገንባት አኳያ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት ለ9 ሺ ወጣቶች ስልጠናውን ለመስጠት ታቅዷል። እስካሁን ባለው ሂደት ከ2 ሺ 600 በላይ ወጣቶች ስልጠናውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በሀረሪ ክልል በአጠቃላይ 27 ሺ ወጣቶችን ለማሰልጠን እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

ስልጠናውን ለመውሰድ በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ

https://ethiocoders.et

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ