+251118132191
contact@mint.gov.et
ስታርታአፖች በየሙያ መስኩ ላይ የታዩ ችግሮችን በመፍታት ግልፅ፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ የዲጂታል መድረክ መፍጠር ይኖርባቸዋል። ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ባይሳ የጨረታ ስርዓት በማዘመን በዲጂታል ጨረታዎች ላይ የተሰማራውን ኦክሽን ኢትዮጵያ የተሰኘውን ስታርትአፕ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ ስታርታአፖች በየሙያ መስኩ ላይ የታዩ ችግሮችን በመፍታት ግልፅ፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ የዲጂታል መድረክ መፍጠሩን ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ሌሎች የፈጠራ ባለሞያዎች እንደዚ መሰል ያልተሰራባቸውን መስኮች በመምረጥ ሊሰሩ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የጨረታን አድካሚ ሂደትን በመገንዘብ ስራውን ቀለል ያደረገ መሆኑን አንስተው ተደራሽነቱን በማስፋት የሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የድርሻውን ለመወጣት እንዲሰራ ተናግረዋል።
የኦክሽን ኢትዮጵያ አላማዎች የባህላዊ የጨረታ ሂደት ላይ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ የጨረታ ስርዓት በመገንባት በመስራት ላይ የሚገኝ ስታርትአፕ ነው።
በጉብኝቱ ላይ አክሽን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ከ32,000 በላይ ተጫራቾች ያሉት እንዲሁም 1.5ቢሊዮን ብር የሚገመቱ ንብረቶች በኦክሽን ኢትዮጵያ ኘላትፎም ለጨረታ ቀርበው መሸጣቸውን የስታርት አፑ መሰራች ወጣት ዮሴፍ አንኩ ተናግሯል።
ወጣት ዮሴፍ አንኩ በአመት 10,000 እና ከዚያ በላይ ወጣቶችን ስለዲጅታል ጨረታ በማሰልጠን ወደስራ እንዲገቡ መደረጉን አንስቷል።
ዋና ስራ አስኪያጁ ጉብኙቱ በተሰማራንበት ዘርፍ ጠንክረን እንድንሰራ የሚያስችል ነው ያሉ ሲሆን አገራችን የተያያዘችውን የዲጂታል ኢትዮጲያ 2025 ጉዞ ለመተግበር መንግስት በፈጠረው ምቹ አጋጣሚ ስታርታአፑ ወደ ገበያ መቀላቀሉን ገልጸዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች