+251118132191
contact@mint.gov.et
ስታርታፕች ውጤታማ ስራ ፈጣሪዎች እየሆኑ ነው።ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ባይሳ የአፍሪካ የግብርና ምርቶች ዲጂቲል ሞል የመሆን ርዕይን በመያዝ በመስራት ላይ የሚገኘው ችፕችፕ (ChipChip)የተሰኘው ስታርትአፕ ጎብኝተዋል።
ሰታርታፑ ከተመሰረተ 11 ወር ገደማ የሆነው ሲሆን ማህበራዊ ግብይትን በማበረታታት ቀጥታ ከማሳው በመረከብ በዲጂታል ገበያ ፕላትፎርም በቅናሽ ለማህበረሰቡ የሚያቀርብ ነው።
ይህ በኢኮመርስ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ላይ እየሰራ የሚገነው ቺፕቺፕ ገበሬዎችን በቀጥታ ከሸማቾች ጋር የማገናኘት ተልዕኮ ይዞ የተመሰረተ ሲሆን በድርጅቱ የተፈጠሩ መተግበሪያዎችን በመጠቀም በግሩፕ የሚገዙ ሰዎችን ያበረታታል።
በአሁኑ ስአት ለ117 ሰዎች ቀጥታ የስራ እድልን የፈጠረ ሲሆን ከ10ሺህ በላይ ሰዎች በተዘዋዋሪ ከዚህ ስታርትአፕ ጋር ይሰራሉ።
ስታርታፑን የጎበኙት ዶ/ር ባይሳ በዳዳ መንግስት ምቹ ስነ-ምህዳርን በመፍጠር ረገድ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን አንስተው ስታርታፕች የማህበረሰብን ህይዎት ከሚያቀሉ ስራዎቻቸው በተጨማሪ ውጤታማ ስራ ፈጣሪዎች እየሆኑ ነው ብለዋል።
ሚኒስትር ድኤታው አያይዘውም የችፕችፕ አባላት የሀገርና የማህበረሰብን ፍላጎት የተገነዘቡ ስራዎችን በመስራት መሆናቸውን ጠቅሰው ለሌሎች ስታርትአፖች አርአያ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።
ስታርትአፑ በቅርቡ ኦስትርያ በተካሃደው ውድድር ከ830 ተወዳዳሪዎች ውስጥ ኡጋንዳንና ካሜሮንን በመከተል ኢትዮጵያን ወክሎ ሶስተኛ በመውጣት የ250ሺ ዶላር ማሸነፉን ዋና ስራ አስኪያጅ ወጣት አሚር ሬድዋን ተናግረዋል።
ወጣት አሚር በቀን ከ3 ሺህ በላይ ትዕዛዞችን እንደሚያስተናግዱ የተናገሩት ሲሆን ከ70ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች እንዳላቸው እንዲሁም በአመቱ 780ሺህ ዶላር በድርጅታቸው ማንቀሳቀሳቸውን አንስተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች