+251118132191
contact@mint.gov.et
በሀገራችን የቴክኖሎጂውን አገልግሎት የበላይነት ለማረጋገጥ በእውቀት ላይ የተመሰረተ በምርምርና በፈጠራ የሚመራ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ተመራማሪዎች በአካልና በኦንላይን ለሶስት ቀን የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ በምርምር ዘርፉ ላይ ለተሰማሩ አካላት የአቅም ማጎልበቻ በመስጠት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ያለመ ነው፡፡
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ አለም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ በሚያከናውኑት ምርምር እያደገና እየተወሳሰበ ባለበት ደረጃ እኩል ለመራመድና ተጠቃሚ ለመሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ እውቀትን ልንጋራና ልንጠቀምበት የምንችልበትን እድል መፍጠሩ አስገዳጅ ሆኗል ብለዋል፡፡
ኢትዩጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ብዙ አቅም እንደነበራት ቀደምት ታሪኮቿ ይናገራሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ዛሬ ለዘርፉ ትኩረት የሰጡ ሀገራት በኢኮኖሚ እድገት ግንባር ቀደም መሆናቸውን ስናይ እኛ ራሳችንን ልንጠይቅና ዘርፉን እስትንፋሳችን አድርገን ልንጠቀምበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በሀገራችን ዘርፉን ለማሳደግ መሰረተ ልማት ከመገንባት ባሻገር ከኢንዱስትሪ፣ ከዩኒቨርስቲ፣ ከምርምር ተቋማት ጋር በትብበር ውጤት ለማምጣት የሚያስችሉ ስነ-ምህዳሮች ላይ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ በሀገራችን የምናካሂዳቸው ምርምሮች ብዙ የማህበረሰባችንን ችግር ከመፍታትም አልፈው የኢኮኖሚ እድገታችን ዘመኑን የዋጁ እንዱሆኑና እንዲፋጠኑ ለማድረግ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል፡፡
ምርምር ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ዘርፍ ቢሆንም ይዞት የሚመጣው ውጤት ችግር ፈቺ ነው ያሉት የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚው የዘርፉ ተዋናዮች የተገኘውን ልምድ በመውሰድና በመጠቀም ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ማዋል የሚቻልበትን ስራ በመስራት አሻራ ሊያስቀምጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው በምርምር ፕሮጀክት አፃፃፍ፣ በስታቲክስ ዘዴዎችና ሌሎች ጉዳዮችን ማዕከል አድርጎ የሚሰጥ ሲሆን ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገራት በዘርፉ ትልቅ አቅምና ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እየተሰጠ ይገኛል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች