+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሀገራችን የኢሌክትሮኒክስ ቆሻሻ የማህበረሰባችን ችግር እንዳይሆን በአያያዙና በአወጋገዱ ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ አሳሰቡ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ የዘርፉ ተዋናይ ከሆኑ ተቋማት ጋር የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ የሚያስችል የሦስት ቀን የባለድርሻ አካላት መድረክ አካሂዷል።

መድረኩ በአለም ላይ ብሎም በሀገራችን ከፍተኛ አደጋ እየጋረጠ ያለውን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ስርዓት ለመፍጠር ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በሀገራችን የኤሌክትሮኒክ ቆሻሻ ወደ አፈርና የውሃ ስርዓታችን ውስጥ ዘልቀው ሊገቡ የሚችሉ አደገኛ ቁሶችን የያዘ በመሆኑ በሰው ጤና እንዲሁም በስነ-ምህዳራችን ላይ ከፍተኛ አደጋን ያስከትላል ብለዋል።

የማህበረሰባችን የኑሮ ዘይቤ ላይ አደጋ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች ቀድመን መከላከል አለብን ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ከሳይንስና ቴክኖሎጂ አንፃር ፈጠራ መፍጠር ብቻ ሳይሆን የተፈጠሩ ነገሮች ምን ያህል ዘላቂ እና ከአካባቢ ጋር ተስማሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ቴክኖሎጂን መፍጠር ሀብት ቢሆንም አያያዙና አወጋገዱ ላይ ሚዛኑ ሊጠበቅ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በቴክኖሎጂ እንድታድግ እየታተርንላት ያለችው ኢትዮጵያ ለሁሉም የምትመችና እኩል ተጠቃሚነት የሚረጋገጥባት ሀገር እንድትገነባና የዓለም ህዝብ ለኑሮ የሚመኛት እንድትሆን የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ለመፍጠር መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽንና የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክቶች ዳይሬክተር አቶ ተሰማ ገዳ ሀገራዊ ኢኮኖሚ ለማጎልበት የሚያስችል በኢትዮጵያ የዲጂታልና የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳርን ግንባታ ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አስገንዝበዋል።

በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ዳይሬክተሩ ለሀገራዊ የዲጂታል ስኬት በሀገር ውስጥ የሚመረቱና ከውጪ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ ወይም ብልሽት ሲገጥማቸው የሚወገዱበትን ስርዓት ለመፍጠር እየሰራን ነው ብለዋል።

በመድረኩ የትምህርት ሚኒስቴር ፣የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ የፅዳት ኤጀንሲ፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፣ የስደተኞችና ስደት ተመላሽ አገልግሎት እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል።

በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች የተሰጣቸውን ቀጣይነት ያለው ተልኮ ከማሳካት ባለፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ