+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሀገራችን የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ባለሙያዎች ሀሳባቸውን ወደ ውጤት መቀየር የሚስችል የአቅም ግንባታ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቢዝኬ የኢንኩቤሽን ማዕከል ከኮሪያ አለም ዓቀፍ ተራህዶ ድርጅት፣ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከአዳማ ዙሪያ ለተውጣጡ የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው በሀገራችን የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ባለሙያዎች ወደ ምርት መግባት የሚያስችል አቅም በመገንባት በቀጣይ የሀብት ባለቤት የሚሆኑበትን እድል ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

በስልጠና መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ልጅአለም አየለ በሀገራችን ያሉ የፈጠራ ሀሳብ ባለሙያዎችን ለነገ ስንቅ የሚሆን እውቀት በማስገንዘብ ሀሳባቸውን ወደ ውጤት በመቀየር ከራሳቸው አልፈው ሀገራቸውን የሚጠቅሙበት እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በቀደመው ዘመን ሀገር መቀየር የሚችሉ የፈጠራ ሀሳብ የነበራቸው ባለሙያዎች የሚደግፋቸው አጥተው መንገድ ላይ ቀርተዋል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በአሁን ሰዓት እድለኛ የሆነው ትውልድ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየተፈጠረ ባለው ምቹ ስነምህዳር በመጠቀም ሀሳባቸውን ወደ ውጤት በመቀየር የተገኘውን እድል ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል፡፡

ሁሉም ሰልጣኞች ስልጠናውን በሚገባ እንዲከታተሉና ያገኙትን እውቀት በመጠቀም የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች በማለፍ ሀሳባቸውንና አላማቸውን ለማሳካት መትጋት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በስልጠና ሂደት ውስጥ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሶስት ተወዳዳሪዎች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጣቸውና ሌሎች ክልሎች ላይ ስልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ