+251118132191
contact@mint.gov.et
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ የተከልናቸውን ችግኞች እንደሰው ልጅ ተንከባክበን ልናሳድጋቸው እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሃግብር እየተካሄደ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራርና ሠራተኞች ከማለዳው 12፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ በአይሲቲ ፓርክ በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እያካሄዱ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን እቅድ እውን በማድረግ ሀገራችን የአረንጓዴ ልማት ተምሳሌት እንድትሆን ሁላችንም የሚጠበቅብንን በመትከል የተያዘውን እቅድ ማሳካት ይኖርብናል ብለዋል።
ችግኝ መትከል ለነገው ኢኮኖሚ እድገት መሰረት መጣል ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ የተሻለች ሀገር ለመገንባት ለምናደርገው ሁለንተናው የልማት ስራዎች መሰረት የሚሆኑ በሁሉም ስፍራ የአረንጓዴ አሻራዎችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን እንደሰው ልጅ መንከባከብና ማሳደጉ ትኩረት የሚሻው መሆኑን በአፅንኦት የገለፁት ሚኒስትሩ ሀገራችን ከዘርፉ ለማግኘት የሚያስችላትን ውጤት እንድታገኝና የማንሰራራቱ ራዕይ ስኬታማነት እንዲረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት ቀደም ብለው በተለያዩ አካባቢዎች የጀመሩትን ችግኝ የመትከል መርሀ ግብሩ በማጠናከር ቀጣይነት እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በፕሮግራሙ ላይ የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩርያ እና ሚኒስትር ድኤታ የነበሩት ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ከተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች