+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የሱፐርቪዥን ድጋፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ከኢንፎርሚሽን መርብ ደህነነት የተወጣ ቡደን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ አተገባበር ላይ የሱፐርቪዥን ድጋፍ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡

የሱፐርቪዥን ድጋፉ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን አላማ ለማሳካት፣ የዲጂታል ክህሎት ለማጎልበትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

የሱፐርቪዥን ድጋፉ ቡድን አባላት በሀገራችን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መንግስት የፈጠረውን ልዩ እድል በመጠቀም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ስራዎችን በመስራት ዜጎች ከራሳቸው አልፈው ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ የሚያስችል ፕሮግራም በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በሀገራችን የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎት ላይ የላቀ አቅም ከመፍጠርም አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የምስክር ወረቀትና የስራ እድል ስለሚፈጥር ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል ተብሏል፡፡

በከተማው የ 5 ሚልየን ኢትዮ ኮደርስን ውጤታማ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን ሂደት ለሱፐርቪዥን ቡደኑ ያብራሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭን ስኬታማ ለማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአስራንዱም ክፍለ ከተሞች ሰፋፊ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሆኑም ገልፀዋል፡፡

የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በሀገሪቱ የተቀመጠለትን አላማ እንዲያሳካ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እየተካሄደ ያለው የሱፐርቪዥን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ክፍለ ከተሞች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን የሱፐርሺዝን ቡድኑ የከተማ አስተዳደሩ የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ አተገባበር ሂደቱ ላይ የተለያዩ ጥያቂዎችን አንስቶ ውይይትና ማብራርያ ተሰጥቶበታል።

በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የሱፐርቪዥን ድጋፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ