+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሃሳብ የተጀመረው ጥረት ወደ ሚሊየነር የሀብት ባለቤትነት…

በኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የተመራው ቡድን በሀገራችን ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም በመፍጠር ላይ ካሉት ስታርታፖች ግሪን ቢን ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘው ODM (ኦሪጅናል ዲዛይንና ማኑፋክቸሪንግ) ጎበኘ።

ጉብኝቱ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድጋፍ የተደረገላቸው ስታርታፖችን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የሚፈለገው ውጤት ላይ እንዲደርሱ ለማስቻል ያለመ ነው።

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ ያላትን የሰው ሀብትና እምቅ አቅሟን ወደ ሀብት መቀየርና መጠቀም እንደምትችል ግሪን ቢን ማኑፋክቸሪንግ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አንዱአምላክ መሀሪው ያሉ የፈጠራ ጀግኖችን እናበዛለን ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን ለፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠረችውን እድል ተጠቅመው የስራ እድልና የማህበረሰባችንን ችግር ከመፍታትም አልፈው የብዙ ሀብት ባለቤት እንዳደረጋቸውም ገልፀዋል፡፡

የግሪን ቢን ማኑፋክቸሪንግ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዱአምላክ መሀሪው ከዜሮ ሀብት መነሻ ተነስቶ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘው የገንዘብ ሽልማት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሀብት ባለቤት እንዳደረገው ተናግሯል።

ችግር ፈቺ ፈጠራዎች ላይ በማተኮር ከ46 በላይ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማሽነሪውችን ነድፎና አምርቶ ወደ ስራ ማስገባቱንም ገልጿል።

የፈጠራ ስራው ለሀገሪቷ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ በሚያሳድሩ ዘርፎች በመመስረት እንደ ቡና ማድረቂያዎችን፣ የእርድ ፖሊሸሮችን፣ የቡና መቁያ እና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ላይ ትኩረቱን አድርጎ መሰራቱን ጠቁሟል ።

ዘርፉ ላይ በመሰማራት የተገኘው የኢኮኖሚ እድገትና የተፈጠረው የስራ እድል እጅግ የሚደነቅና የሚበረታታ በመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጎብኝዎች ገልፀዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ