+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በህግ አወጣጥ ሂደት የህዝብና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ምክክር ስርዓት (E-consultation Portal) ይፋ ሆነ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከጀርመን ልማትር ድርጅት GIZ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በረቂቅ ህግ ላይ የኤሌክትሮኒክ ምክክር ስርዓት መተግሪያ (E-consultation Portal) ይፋ ሆኗል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በሕግ ዝግጅት ሂደቱ የፍትህ ተቋማት የህዝብና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማረጋገጥ መስራት የሚገባቸው መሆኑን ጠቁመው ይህም የመንግስትን አሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት ማሳያ እና የህገ-መንግስት መርሆችን ተግባራዊ የማድጊያ አበይት መንገድ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በህግ ዝግጅት ሂደት የህዝብን ተሳትፎ ማረጋገጥ የሚወጡ ህጎችን ጥራት ማሰጠበቅ ከማስቻሉም በላይ በአተገባበር ሂደትም የህዝብ ቅቡልነት ያለው በአግባቡ የሚተገበር ህግ እንዲሆን ያስችላልም ብለዋል።

ከዚህ አንፃርም ረቂቅ ህጎች ሲዘጋጁ ከህበረተሰቡ ግብዓት የሚሰባሰብበት ስርዓት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ መዘጋጀቱ የህዝብና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚያረጋግጥ እና ተዓማኒነቱን ከፍ የሚያደርገው መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ የኤሌክትሮኒክ ምክክር ሥርዓቱ ከዜጎች፣ ከሕዝቡ፣ ልዩ ፍላጎት ካላቸው ዜጎች፣ እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች አስተያየቶችን ለመቀበል የሚያስችል አዲስ መድረክ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኤሌክትሮኒክ ምክክር ስርዓት መተግሪያው (E-consultation Portal) ሰፊ ተደራሽነትን በመፍጠር ተጨማሪ ተሳትፎን የሚያበረታታና ግልጽነትን በመፍጠር ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል እንዲሁም ለሚዘጋጁ ህጎች የተሻለ ተሳትፎና ሃሳብ ለማግኘት የሚያስችል በአነስተኛ ወጪ የሚከናወን ነው ብለዋል፡፡

ስርአቱ በክልል ደረጃም ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጎ የለማ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ መንግስት እንደ ሀገር አሰራሩን በዲጂታል ሥርዓት ለመደገፍ እያደረገው ያለው ጥረት አንዱ መገለጫ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ የጀርመን የልማት ድርጅት ተወካይ ዶ/ር አልቤርቶ ጎሜዝ ተገኝተው ባስተላፉት መልዕክት ይህ የኤሌክትሮኒክ ምክክር ሥርዓት (E-consultation Portal)በአጠቃላይ በህግ አወጣጥ ላይ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የፍትህ ስርዓቱን የሚያግዝና ጠቃሜተው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተሳታፊዎች ባሉበት ሆነው በሚዘጋጁ ረቂቅ ህጎች ዙርያ ሀሳባቸውን የሚያካፍሉበት ይህ የኤሌክትሮኒክ ምክክር ስርዓት መተግበሪያው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ