+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ (Geographical Indications- GI) ስርአት ዙርያ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል

ኮንፍረንሱ የመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ ስርዓት ለዘላቂ ልማት <Establishing GI System for Sustainable Development>በሚል መሪ ቃል ግንቦት 26 እና 27 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

ኮንፍረንሱን ን በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ መድረኩ/ኮንፍረንሱ በኢትዮጵያ የእድገት ጉዞ ወሳኝ ወቅት ላይ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና በአፍሪካ የአእምሮአዊ ንብረትን ጥበቃ ሂደትን ከዚህ በላይ ለማሳደግ ጉባኤው የሚኖረው ፋይዳ ወሳኝ እንደሚሆን የጠቀሱት ሚኒስትሩ በዚህ ፈጣን የእድገት ዘመን የአእምሮ ጥበቃን ተግባራዊ ማድረግ ቅንጦት ሳይሆን ግዴታ መሆኑን የተገነዘቡ ስራዎች እንደሚሰሩም ተናግረዋል/ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ዘርፉን የሚያግዙ ስምምነቶች ጸድቀው ወደ ስራ መግባታቸውን አንስተው ምቹ ስርአትን ከመዘርጋት አኳያ በቅርቡ የተሻሻለው የብሔራዊ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ለፈጠራ እና ለአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ዳይሬክተር ጀነራል ዳረን ታንግ ኢትዮጵያን በአንጸባራቂ ባህሎች እና ቅርሶች እንደ ቡና እና ማር ያሉ ተፈጥሯዊ ምርቶች የታደለች መልካም ምድር ባለቤት መሆኗን ጠቅሰው ድርጅታቸው ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት ጋር ትብብሮችን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችው ጠንካራ ስራ ከሀገሪቱ አልፎ አፍሪካን የሚያነቃንቅ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያስችል እንደሚሆን ጠቅሰው በግብርናው ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎች በተለይም ሀገሪቱ በቡና ሃብት ልማት ላይ ያላትን አቅም አሟጣ ለመጠቀም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

ጉባኤው የተለያዩ ሃገራት ከፍተኛ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ ስርዓት ተሞክሮዎች የሚያቀርቡበት መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል በባለስልጣኑ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ የመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ላይም ውይይት ይካሄዳል ብለዋል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ዳይሬክተር ጀነራል ዳረን ታንግ ድርጅቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችውን እንቅስቃሴ ለማሳደግ በሚያግዙ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በህዝብ ቁጥር ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አንስተው በተለይም ወጣቱን አምራችና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ስራ መሰራት እንዲችል WIPO ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ዳይሬክተር ጀነራል ዳረን ታንግ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችውን እንቅስቃሴ እንድታጠናክር በመግለጽ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ ጉባኤ ላይ የሚነሱ ሃሳቦች ወደ ሰትራቴጂካዊ አጀንዳዎች የሚቀየሩ ሀሳቦች እንደሚወሰዱበት ጠቅሰው ድርጅታቸው ይህንን ለማድርግ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ለመወሰን ከዚህ ጉባኤ ግብአት እንደሚያገኙ ገልጸዋል።

በጉባኤው የተለያዩ የኢትዮጵያ መገለጫ የሆኑ የግብርናና የዕደ ጥበብ ውጤቶች ለጉብኝት የቀረቡ ሲሆን ከአለም አቀፍ የመልክዓ ምድራዊ አመላካች ልምድ እና ማዕቀፍ ውስጥ የቻይና፤ የዩናይትድ ኪንግደም እና የተመረጡ ተሞክሮዋች በዛሬው ውሎ ቀርበዋል ጉባኤው ነገ በሚኖረው ውሎ ም በኢትዮጵያ የጂኦግራፊያዊ አመላካች እድገት የሚገኝበት ደረጃም ይቀርብበታል።

ጉባኤውን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት እና ከ Agence Française de Développement (AFD) ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ