+251118132191
contact@mint.gov.et
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ አፈጻጸም ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ ከሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።
በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራምን ለመከታተልና ለመደገፍ የተቋቋመው የፌደራል ስልጠና ድጋፍና ክትትል ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ አፈጻጸምን ዙሪያ ምልከታውን አካሂዳል።
በተደረገው ምልከታ ክልሉ ስልጠናውን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፈጠር እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
በተለይም በዩንቨርሲቲዎች፣ኮሌጆች ሆስፒታልና ምስል ተቋማት የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ቴክኒካል ድጋፍን የሚጠይቁ እና ሌሎች ተግዳሮቶችን ለመፍታት በክልሉ ከሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የፌደራል ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ድጋፍና ክትትል ቡድን አመላክቷል።
የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችለውን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ በዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች
©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ