+251118132191
contact@mint.gov.et
በምርምር ተቋማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለጹ
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ጥናት ማዕከል /Africa Center of Technology Studies (ACTS/ በፋይናንስ የሚደገፉ 6 የጥናት ምርምር ፕሮጀክቶች ግምገማ እና የመማሪያ አውደ ጥናት ተካሄዷል፡፡
በዝግጅቱ ተመራማሪዎች በየተሰማሩባቸው የጥናትና ምርምር መስኮች ሳይንሳዊ የሆኑ ምርምሮችን በማካሄድ በተግባር ልምምድ የተደረሰባቸውን ውጤታማ ሥራዎች ከናሙና ጋር በአወደ ርዕይ መልክ አቅርበው ተጎብኝተዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ ለምርምር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራች መሆኗን ጠቅሰው ይህንን ወጤታማ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች የምርምር ተቋማትን በመገንባት እየሰራች እንደምትገኝ ጠቁመዋል።
በተቋቋሙት የምርምር ተቋማት እና በሀገር ውስጥ ሙህራን በተሰሩ የምርምር ስራዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተገኙ ያሉ ውጤቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
በምርምር ዘርፍ ያሉ ውጤታማ ልምድና ተሞክሮዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሀገር ውስጥ አቅምን አስተባብሮ ከመጠቀም ባለፈ አለም አቀፍ ትብብርን የሚያጠናክሩ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አንስተዋል።
የምርምር ውጤቶችን አምርቶ በስፋት ወደ ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ በወርክሾፑ የተነሳ ሲሆን የግል ባለሀብቶች በምርምር ድጋፍ ዙርያ ተሳትፎ ማነስ ችግሩን እያባባሰው እንደሆም ተጠቅሷል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በሀገራችን ባለፉት 6 ዓመታት በዘርፉ የተከናውኑ 20 የጥናት ምርምር ሥራዎች በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ጥናቶች ማዕከል (ACTS) በፋይናንስ የሚደገፉት የማህበረሰብን የኑሮ ሁኔታ በማቃለል ችግሮችን እንደሚፈቱ ጠቁመዋል፡፡
የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል፣ ለማሳደግና ለገበያ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥናቶችን፣ የምርምርና ስርፀት ሥራዎችን የማበረታታት እና ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጠው ተልዕኮ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሀገራዊ የምርምር አሰተባባሪ በሆነው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በርካታ ምርምሮች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ተመራማሪዎች አዳዲስ ምርምሮች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩም ጠይቀዋል።
በአውደርዕዩ ላይ ቆሻሻን ወደ ሀብት ቴክኖሎጂ ማሻሻል (የባዮጋዝ ተክሎች አቀማመጥ ቁፋሮ እና ጡብ ማምረት)፣ ፍራፍሬዎችን ለማጓጓዝ እና ለማከማቸት ማሸግ፣ ከቲማቲም ግንድ የቆሻሻ ጥራት ያለው ምርት የማውጣት ሂደት፣ ጥሬ ዕቃውን በመቁረጥ የእርሻ ቆሻሻን ወደ የእንስሳት መኖ የሚቀይር የመኖ ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ ልማት፣ ከኢንዱስትሪ ዝቃጭ ከZeolite-Synthesized በመጠቀም የናኖ ማዳበሪያ ማምረት እና ለእንሰሳት መኖ የሚሆኑ የበሰበሱና በፈንገስ የታከሙ የሰብል ቅሪት ማዘጋጀት የተሰኙ የምርምር ውጤቶች ቀርበዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች