+251118132191
contact@mint.gov.et
በምስራቅ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ለውጥ ለማምጣት ያለመው የባዮቴክኔት (BioTechNet) 2ኛ ምዕራፍ ማስጀመሪያ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ።
በኢትዮጵያ የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና በዓለም አቀፉ ICGEB ትብብር የተዘጋጀው የባዮቴክኔት (BioTechNet) ሁለተኛ ምዕራፍ ማስጀመሪያ ጉባኤ፣ “በምስራቅ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር “ በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በመክፈቻው ላይ እንደገለጹት፣ ድንበር ተሻጋሪ ችግሮችን ለመፍታትና የጋራ ብልጽግናን ለማምጣት ቀጣናዊ ሳይንሳዊ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
የባዮቴክኔት የመጀመሪያ ምዕራፍ በሰው ኃይል ልማትና በምርምር መሰረተ ልማት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን በማስመዝገብ ለጤናና ለምግብ ዋስትና መሰረት መጣሉን ሚኒስትር ዴኤታው አስታውሰዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ አዲሱ ምዕራፍ ከአቅም ግንባታ ባለፈ የፖሊሲ አውጪዎችንና የፈጠራ ባለሙያዎችን በማስተሳሰር ትልቅ ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ሳይንሳዊ ግኝቶችን ከማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ፍላጎቶች ጋር በማገናኘት ምርምሮችን ወደ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እሴት ለመቀየር ኢንስቲትዩቱ በትጋት እንደሚሰራ ፕሮፌሰሩ አረጋግጠዋል።
ከኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ የተውጣጡ ሳይንቲስቶችና አመራሮች ቀጣናውን የባዮቴክኖሎጂ የፈጠራ ማዕከል ለማድረግ በጋራ መክረዋል።
ጉባኤው የቀጣናውን የጤናና የምግብ ዋስትና ችግሮች ለመፍታት በሚረዱ የዕፅዋትና የጂኖሚክስ የጋራ ምርምር ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልዷል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች