+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በምስራቅ አፍሪካ የመጀመርያ የሆነው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025)

በኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተከፈተው እና በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የዘርፉ ምሁራን በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል።

በኤክስፖው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲደግፋቸው ከነበሩ ስታርታፖች ውስጥ በማወዳደር 30 ስታርታፖች በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ(ETEX2025)እንዲሳተፉ ተደርጓል።

ሃገራችን ለዘርፉ በሰጠችው ትኩረት የቴሌኮም አገልግሎቶች እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች፣ ዲጂታል መታወቂያ፣ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፣ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራዎች፣ የስማርት ከተማ ልማት የመሳሰሉት በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ መሰረት የሚጥሉ ስራዎች ያመጧቸው ተጨባጭ ማሳያዎች በኤክስፖው እየተጎበኙ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለሰጠችው ትኩረት እና ቁርጠኝነት ማሳያ የሆነው ይህ አለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ የሳይበር ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI)፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ስማርት ከተሞች፣ ስታርታፖች እና የቴክኖሎጂ ክህሎት ባሉ ወሳኝ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።

ከግንቦት 8 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው ኤክስፖ በዘርፉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች ከመላው ዓለም የተውጣጡ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ መሪዎችና ምሁራን በስፋት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በኤክስፖው በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና ድርጅቶችን ክቡር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊወች ጎብኝተውታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ