+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሩብ ዓመቱ የአእምሯዊ ንብረት መስፈርቶችን ላሟሉ ከ1 ሺህ 300 በላይ ጥያቄዎች የፈቃድ ማረጋገጫ ተሰጥቷል

በሩብ ዓመቱ የአእምሯዊ ንብረት መስፈርቶችን ላሟሉ ከ1 ሺህ 300 በላይ ጥያቄዎች የፈቃድ ማረጋገጫ መስጠቱን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአእምሯዊ ንብረት ምንነት፣አስፈላጊነትና የጥበቃ ስርዓትን በሚመለከት ከክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማትና ኤጀንሲዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባና ጥበቃ ግንዛቤን በማሳደግ በተደራጀና በተናበበ መልኩ በትብብር ለመስራት ዓላማ ያደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ኤሊያስ ሙሀመድ ባለስልጣኑ የንግድ ምልክት፣የፈጠራ ባለቤትና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲጠበቁ ይሰራል ብለዋል፡፡

በዚህም የአሰራር ማሻሻያ በማድረግና የቴክኖሎጂ አሰራር በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የፈጠራ ስራና የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ መደረጉ የፈጠራ ባለቤቶች ተወዳዳሪና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያበረታታ እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህም በሩብ ዓመቱ በንግድ ምልክት፣በፓተንት፣የቅጅና ተዛማጅ መብቶች መስፈርት ላሟሉ ከ1 ሺህ 300 በላይ ጥያቄዎች የፈቃድ ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡

ይህንን መሰል ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተሳታፊዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

Website www.mint.gov.et

Facebook

https://www.facebook.com/MInT.Ethiopia?mibextid=ZbWKwL

Telegram

https://t.me/MinTEthiopia

LinkedIn

https://www.linkedin.com/.../ministry-of-innovation-and.../

(X) Twitter

https://x.com/MinistryofInno2?t=kM3bILU4XM7m0GVjnahnwA&s=09

YouTube channel https://www.youtube.com/@MinistryofInnovationandTechnol

TikTok

https://www.tiktok.com/@ethiopianm

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ