+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ዲጂታል ዘርፉ ላይ አለም አቀፍ እውቅና ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ።

በግዕዝ ትምህርትና ስልጠና ድርጅት እና በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ በ275 ኮርሶች ላይ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተካሂዷል።

ስምምነቱ በአለም አቀፍ ደረጀ በተግባር ብቁና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና ለመስጠት ያለመ ትብብር ነው።

በስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ተማሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የትምህርት ማስረጃዎች፣ ዕውቀቶችን፣ ተግባር ላይ የተመሰረቱ ችሎታዎች በማጎልበት በየጊዜው እየተለዋወጠ ያለውን የአለም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመምራት በሚያስችል ራዕይ ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በአይሲቲ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመቀበል በዲጂታል አብዮት ጫፍ ላይ ትገኛለች ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የትብብር ተቋሙ በክህሎት ልማት ላይ የሚደረግን ኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የፋይናንሺያል እና ዲጂታል ገበያዎች ውስጥ በምታደርገው ሚና ላይ ጭምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገለግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው በመምጣት እንደዚህ ያለ እድል በመፍጠር ያላቸውን እውቀት በማጋራት የድርሻቸውን እየተወጡ ነው ብለዋል፡፡

በሀገራችን የሌሉ በውጪ ሀገራት ያሉ ባህሎችን፣ እውቀቶችንና የአሰራር ስርዓቶችን ወደ ሀገራችን እንዲመጡና እንድንጠቀምባቸው የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የኢኮኖሚ እድገታችን ማገዝ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡

የእያንዳንዱን ተቋም ጥንካሬ በማጣመር ለእውቀት ሽግግር፣ ለአቅም ግንባታ እና ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጠንካራ መሰረት ለመጣል መሰራት እንዳለበት በፕሮግራሙ ላይ ተነስቷል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ