+251118132191
contact@mint.gov.et
በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ኢንጂነሪንግ እና ማትስ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት የሚያግዝ ስልጠና ከመላ ሀገሪቱ ለተወጣጡ ሴቶች እየተሰጠ ነው።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሴቶችን ተሳትፎን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ኢንጂነሪንግ እና ማትስ (STEM) ላይ ለማጎልበት የሚያግዝ ስልጠና ከመላ ሀገሪቱ ለተወጣጡ ሴቶች እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው ሴት ተማሪዎችንና መምህራንን በሳይንስ፤ በሥነ ፈለክ ማበረታታት(SciGirls - Empowering Girls and Female Teachers in Science Through Astronomy)በተሰኘ ፕሮጀክት ለሁለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎችና ሳይንስ መምህራን የሚሰጥ ነው፡፡
በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየው የሴት ተማሪዎች በተለይም በSTEM ዙሪያ ያላቸውን ተሳትፎ፤ እውቀትና መነሳሳትን ማሳደግና በቀጣይ በሳይንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሚንስትር ዴኤታው ሴቶች ዘርፉን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ ያላቸውን አቅም በመጠቀም የድርሻቸውን እንዲወጡ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ቤተልሄም ንጉሴ(ኢ/ር) ኢንስቲትዩቱ ሴቶችን በSTEM ላይ ብቁ ተሳታፊና ተወዳዳራ እንዲሆኑ የተለያዩ ስልቶችንና ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በስልጠናው የሚሳተፉት ሴት ተማሪዎች ከዋና ከተሞች እርቀው የሚገኙ እና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ከ9ኛ-10ኛ ክፍል የሆኑ የ2ኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎችና የሴት የሳይንስ መምህራን መሆናቸውንም ኢንጂነር ቤተልሄም ገልፀዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ሲሆኑ ለተከታታይ 6 ቀናት እንደሚሰጥም ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች