+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ዘርፎች የሚሰሩ ስራዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ሚና እያበረከቱ ነው። ዶ/ር በለጠ ሞላ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስትዩቲት እና በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ማዕከል በመገኘት የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ በተቋማቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ምልከታ በማድረግ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም በተቋማቱ መካከል ተሞክሮ ለመለዋወጥ ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ ነገ ላይ በምድር ብቻ ሳይሆን በስፔስ ላይ የሚኖርን ሀብት መጠቀምና በድርሻችን መቆጣጠር የምንችልበትን እድል ለመፍጠር ዛሬ ያለንን አቅም ሁሉ አሟጠን ቴክኖሎጂውን ማልማትና መጠቀም አለብን ብለዋል።

ዘርፉ ከምድር እስከ ህዋ ያሉ ስራዎችን የሚዳስስ ስፊ አውድ ያለው ነው ያሉት ሚኒስትሩ በሀገራች ካሉ ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ያለውን ትልቅ ሀብት በማጋራት ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምትጠብቀውን ውጤት ለማሳካት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በጉብኝቱ በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ዘርፎች የሚሰሩ ስራዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የላቀ ሚና እያበረከቱ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የሰብል ክትትል፣ የጂኦዴቲክስ መሠረተ ልማት አገልግሎት፣ የከተማ ልማት ክትትል፣ የውሃ ክትትል፣ የገጠር መረጃ ክትትል፣ የአደጋ መከታተያ እና የዲጂታል ካርታ አገልግሎት ማዕከላት በሀገር ደረጃ በየ ዘርፉ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ድጋፍ እያደረጉ መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ወጣት ለማነቃቃትና በዘርፉ የተማረ ትውልድ ለመፍጠር ከዩኒቨርሲቲወችና ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር የጠበቀ ቁርኝት መፈጠር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስትዩቲት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ የሁለት ተቋማት ውህደት ላይ ስኬታማ ስራዎችን በመስራት እንደሀገር ያቀድናቸውን በተሳካ ሁኔታ እያከናወንን ነው ብለዋል።

አቅም ገንብተን ካልሰራን ማንም አይፈልገንም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከምድር እስከ ህዋ ቴክኖሎጂን የምንጠቀምበት የስራ መስክ በመሆኑ ተቋሙ የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ላይ ስኬታማ እንደነበረ ገልፀው ዘርፍ ትልቅ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል። ።

በሱፐርቪዥኑ ማጠቃለያ ውይይት ላይ ከቡድኑ ገንቢ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ የተሰጣቸው ሲሆን መልካም ተሞክሮዎችን ሁሉም ተቋማት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ