+251118132191
contact@mint.gov.et
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በ15 ዋና ዋና ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከአገራዊ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር የትግበራ ሂደት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
በዕለቱም በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የሚመራው አገራዊ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት አስተባባሪ ኮሚቴ በስፔስ ሳይንስ እና ጂስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት እስካሁን ያሉትን አፈጻጸም ተገምግሟል።
ክቡር ሚኒስቴር ዴታው የዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን በመግለጽ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን አድንቀው፣ ክንውኖቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ፤ በ10 ዓመቱ የተያዘውን እቅድ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያድርግ መሆኑን ገልጸዋል።
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ በግልጽ እንደተመላከተው የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት በትኩረት ከሚሰሩ ዘርፎች አንዱ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት ሃገራዊ አጀንዳ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከአጋር አካላት ጋር በመሆን እስካሁን ድረስ በ15 ዋና ዋና ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት መዘርጋት የጀመረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሰባቱ ከተሞች በመጠናቀቅ ላይ ሲሆኑ በመጪው ጊዚያት ከከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በትብብር 18 አዳዲስ ከተሞች ላይ ሥርዓቱን ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑንም ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች