+251118132191
contact@mint.gov.et
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ዘርፍ ክልሎችን በንቃት የሚያሳትፍ ቅንጅታዊ አሰራር ይተገበራል
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ዘርፍ የሚሰሩ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ክልሎችን በንቃት የሚያሳትፍ ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚተገበር በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ገልጿል።
በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
በተለይም ኢንስቲትዩቱ ዘርፉ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት የሚኖረውን አበርክቶ ለማሳደግ ከክልሎች ጋር በሚሰራቸው እቅዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ዘርፍ የሚሰሩ የምርምር ስራዎችና የሚወጡ መረጃዎች የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ፣ልማትን ለማፋጠንና በመልካም አስተዳደር ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አቅም የሚፈጥሩ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ ገልጸዋል።
የሀገሪቱን የጂኦስፓሻል መረጃ በአንድ ተቋም አቅም ማደራጀትና መረጃዎችን በየጊዜው ማስተካከል አዳጋች በመሆኑ ክፍተቱን ለመሙላት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የመስራት ልምድን ማጎልበት ይጠይቃል ብለዋል።
ይህም እውን እንዲሆን ኢንስቲቲዩቱ ከምንጊዜውም በተሻለ ክልሎችን የሚያሳትፍ ቅንጅታዊ አሰራር ለመዘርጋት ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ቤተልሄም ንጉሴ በበኩላቸው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከክልሎች ጋር የሚሰሩ ተግባራት ተለይተው ተቀምጠዋል ብለዋል።
ተቋሙ የታዳጊዎችን የቴክኖሎጂ አቅም የማሳደግና በኢንስቲትዩቱ የለሙ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ክልሎች በሚያሳዩት ፍላጎት መሰረት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በተጨማሪም ክልሎች የሳተላይት መረጃዎችን እንዲያገኙ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሱሌማን እሸቱ እና የደቡብ ኢትዮጵያ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አፈወርቅ ለማ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ትብብሩ በክልሎቹ የሚገኙ የመሬት ሃብቶችን በአግባቡ ለማስተዳደርና የዘመነ አሰራር እንዲኖር የሚያስችል አቅምን የሚያጎለብት መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች እንደ ሀገር ተጨባጭ ለውጥ እንዲያስመዘግቡና መሰረተ ልማቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ሃላፊነታችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ብለዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች