+251118132191
contact@mint.gov.et
በብሄራዊ የአእምሯዊ ንብረት ሳምንት የህግ አውጭዎች ሴሚናር ተካሂዷል።
ከዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት እና ከጃፓን ፓተንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር እየተካሄደ በሚገኘው ብሄራዊ የአእምሯዊ ንብረት ሳምንት የዘርፉን ባለሞያዎች ያሳተፈ የህግ አውጭዎች ሴሚናር ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ፎዚያ አሚን (ዶ/ር) በ10 ዓመቱ ዕቅድ ኢኖቬሽን፣ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል አገልግሎት ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አውስተው ለፈጠራዎች መበረታታትና የስራ ዕድል ፈጠራ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ስርዓት ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም ለዘርፉ በቂ ትኩረት መስጠትና ባለስልጣኑ እያከናወናቸው የሚገኙ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያና፣ ሌሎች የሪፎርም ስራዎችን መደገፍ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ፎዚያ አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመስል ኢትዮጵያ ሃገራዊ የቴክኖሎጂ አቅሟ እንዲያድግ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ቴክኖሎጂያዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ የአዕምፘዊ ንብረት ስርዓት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው ብለዋል።
እያይዘውም በህግ ማዕቀፍና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ስራዎች ላይ የህግ አዉጭዎች እና የባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት የአፍሪካ ዲቪዥን ተጠባባቂ ዶ/ር ሎሬታ አሲዱ እና የአለም አቀፍ ክላሲፊኬሽንና ስታንዳርድ ዲቪዥን ዶ/ር ኩኒኮ ፉሺማ በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ስራዎች የህግ ማዕቀፎች የሚኖራቸው ፋይዳና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ንግግር አድርገዋል።
በዝግጅቱ ላይ የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ስምምነት እንዲሁም የማድሪድ ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት ምዝገባ ፕሮቶኮል መተግበርያ አዋጆችን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሰሞኑን ማጽደቁ ለዘርፉ እመርታ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዓለም ንግድ ድርጅት እና ተያያዥ የዓለም ስርዓት ውስጥ በመግባት የዘርፉን ሚና ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡
ለህግ አውጪዎችና ባለድርሻ አካላት በተዘጋጀው ወርክሾፕ የአእምሯዊ ንብረት ስርዓት ዓለም አቀፋዊ ይዘት፣ ልምድ፣ የህግ ማዕቀፍ እና ተግባራዊነትን የሚመለከቱ ውይይቶች ተከናውኗል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች