+251118132191
contact@mint.gov.et
በተለያዩ የምርምር ተቋማት እና ተመራማሪዎች የሚከናወኑ የምርምር ውጤቶች በአእምሯዊ ንብረት መመዝገብ እንዳለባቸው ያለው አረዳድ አናሳ መሆኑ በአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ስራ ክፍተት እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
በተለያዩ የምርምር ተቋማት እና ተመራማሪዎች የሚከናወኑ የምርምር ውጤቶች በአእምሯዊ ንብረት መመዝገብ እንዳለባቸው ያለው አረዳድ አናሳ መሆኑ በአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ስራ ክፍተት እየፈጠረ መሆኑ በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የአእምሯዊ ንብረት ስራ የሀገር ኢኮኖሜ ግንባታ ላይ ጉልህ ድርሻ ያለው እና ኢንቨስትመንትንም የመሳብ አቅም ያለው በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ይህንን በመገንዘብ የተቋሙን አደረጃጀትና አሰራር ስርዓት በማዘመን የሪፎርም ስራዎችን በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ ፤ተቋሙ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች የሚኖረንን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና በንግድ ምልክት፣በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም በፓተንት መብቶች ዙርያ ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሞያዎችን የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል እገዛ ከተቋሙ ይጠበቃል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች ለአእምሯዊ ንብረት ስራ የሚኖረው ሚና ውሳኝ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያም የተወሰኑ አለማቀፍ ስምምነቶችን መፈረሟን ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ የፓሪስ ኢንዱስትሪያል ንብረት ጥበቃ ኮንቬንሽንን እና ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክቶች ምዝገባ ፕሮቶኮልን በአዋጅ ማጽደቋን አንስተው የሪያድ ዲዛይን ህግ ስምምነት ሰነድን መፈረሟን አስታውሰዋል።
ባለስልጣኑ በሀገሪቱ ውስጥ ለአእምሯዊ ንብረት በቂ የህግ ጥበቃ እንዲኖር ለማስቻል ፣በፓተንት ሰነዶች ውስጥ የተካተቱ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ለማደራጀት እና ለማሰራጨት እንዲሁም አጠቃቀሙን ለማበረታታት ይሰራል።
በተጨማሪም በአእምሯዊ ንብረት ላይ ፖሊሲዎችን እና ህጎችን ለማጥናት፣ ለመተንተን እና ለማማከር እንዲሁም በአእምሯዊ ንብረት ዙርያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ስራን እያከናወን ይገኛል።
በንግድ ምልክት፣በቅጅና ተዛማጅ መብቶች፣በፓተንት እና በጂኦግራፊያው ምንጭ አመልካች ምዝገባ ያከናወናቸው ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን የፖተንት፣ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ እና የቅጂ መብት እንዲሁም ተዛማጅ መብቶች አዋጆች በባለስልጣኑ የሚተዳደሩ ናቸው።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች