+251118132191
contact@mint.gov.et
በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጀማሪ ስታርትአፖችን ለመደገፍ የሚያስችል የስልጠናና ውድድር መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጃይካ የኒንጃ ዩኒቨርስቲ ስታርትአፕ ልማት ፕሮግራም እና R&D Group በመተባበር በመቐለ ለጀማሪ ስታርትአፖችን የስልጠናና ውድድር መርሀ ግብር አካሄደ።
በውድድሩ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ በኢኖሼንና ቴክኖሎጆ ሚኒስቴር የስታርትአፕ ልማት ዴስክ ሀላፊ አቶ ታደሰ አንበሴ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያለንን ያልተነካ ፀጋ ወደ ሀብት ለመቀየር ስታርታፕ ስነምህዳር ማስፋትና የስራ ፈጠራን ማበረታታት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ስልጠናው ከመቐለ ዩኒቨርስቲ የተውጣጡ 11 ጅምር የስታርትፕ ሀሳብ ያላቸው ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ጀማሪ የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ተማሪዎች የንግድ ሀሳባቸውን ለማሳደግና የፈጠራ ስራዎቻቸውን ወደ ቢዝነስ እንዲቀየር ትልቅ ድጋፍ የሚያደርግ ነው።
በሽልማቱ ፕሮግራም የትግራይ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር ከላሊ አድሃና እንደሀገር ያለንን ህልም እውን ለማድረግ በእውቀት የሚመራ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢኮኖሚ ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ የስታርትፕ እና ፈጠራ ስራዎች ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።
ውድድሩ በአራት ዩኒቨርስቲዎች ማለትም በመቀሌ ፣በጅማ ፣ በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን በዚህ በሚቀጥለው እመት በተለያዪ ዩኒቨርስቲዎች የሚተገበር ሲሆን በዚህ ውድድር አሸናፊዎች የእውቅናና ለስራቸው የሚያገለግላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች