+251118132191
contact@mint.gov.et
በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማህበረሰቡ በማሳወቅ የዜጎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፌደራል፣ ከክልልና ከከተማ መስተዳዳር ለተውጣጡ የማህበረሰብ አንቂዎች በሚኒስትር መስሪያ ቤቱና በተጠሪ ተቋማት በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን ላይ የማስገንዘብና የማስጎብኘት መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ተደራሽ በማድረግ ማህበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ያለመ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የሀገራችን የኢኮኖሚ ልዕልና ለማረጋገጥ ዛሬ በየስፍራው የሚፈነጥቁ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን ለነገ ብርሃን እንዲሆኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እዳለበት አሳስበዋል፡፡
ዓለምን እየመራ ያለውን የቴክኖሎጂ እውቀት ባለቤት ለመሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየተሰሩ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በዓለም ላይ የሁለንተናዊ እድገት መሰረት የሆነ ጊዜውን የሚዋጅ የቴክኖሎጂ እውቀትን በመታጠቅ የፈጠራ ሀሳቦችን ኩባንያ የሚሆኑበትን እድል ለመፍጠር ልንተጋ ይገባል ብለዋል፡፡
አክለውም በተቋማቱ የሚሰሩ ስራዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ሚና፣ የተገኙ ውጤቶች ያሉበትን ደረጃ፣ ለሀገራችን ብልፅግና ዋና ሞተር ሆኖ ያመጣውን ለውጥና አጠቃላይ ገፅታ ላይ ሰፊ ሀሳብ በማጋራት አስገንዝበዋል፡፡
የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ የሀገራችንን የአኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ አቅም የሚፈጥሩ አዳዲስ የቴክኖሎጂና የምርምር ውጤቶችን በማምረት ወደ ማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከተቋሙ ባለፈ የሌሎችም የማስተዋወቅ ስራ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ሀገራችን በዓለም ላይ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላትን እድል ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች በሁሉም ዘርፍ የዘመነች ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ መገንባት እንደሚቻል ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡
በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን እጅግ አስደማሚ መሆናቸውን ከማየትና ከመደሰት አልፈው ለመጡበት ማህበረሰብ ለማድረስና ለማስገንዘብ የቤት ስራቸውን መሰነቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች