+251118132191
contact@mint.gov.et
በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በሀገር ደረጃ 422,842 ሰዎች ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ዶ/ር በለጠ ሞላ
5 ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በሀገር ደረጃ 422,842 ተመዝግበው ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ተናግረዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በክልሎች ያለውን አተገባበር ሂደት የሚከታተልና የሚደግፍ ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት የተወጣጣ ግብረ-ሃይል አቋቁሟል።
ግብር ሃይሉ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኢንሼቲቩን አፈጻጸም ለመገምገና በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስታት መካከል በተደረገ ስምምነት የተነደፈው ይህ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ እስከ 2026 ለአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የዲጂታል ክህሎት ስልጠና በመስጠት ወጣቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አወንታዊ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው ማስቻልን አላማ ያደረገ ነው፡፡
ለግብረ ሃይሉ መመርያ የሰጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ እና ዳታ ሳይንስ ዘርፎች በፌዴራል እና በክልል መንግስታት በርካታ ሰዎች ስልጠናውን እየወሰዱ መሆኑ ጠቅሰዋል።
ሚኒስትሩ እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በሀገር ደረጃ 422,842 ተመዝግበው ስልጠናውን እየወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰው 104,460 ሰዎች ስልጠናውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
አያይዘውም በ 2026 በሶስት አመት ውስጥ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊን የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ወስደው ሰርቲፋይድ እንዲሆኑ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አወንታዊ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው ከተያዘው ትልም አኳያ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
ይህን ትልም በላቀ ሁኔታ ለማሳካት ከፌዴራል እስከ ክልል ያሉ አመራሮች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተቀናጀ አመራር በመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ይህንን ቅንጅት ለማጠናከር የተቋቋመው ግብር ሃይል ኢንሼቲቩ በክልሎች ያለውን አፈጻጸምና ለስልጠናው የተሰጠውን ትኩረት እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን እንዲለይና በቀጣይ በመንግስት መፍትሄ የሚሹ ጉዳዬችን ለመፍታት የሚያግዝ ስርአት ለመዘርጋት የሚረዳ ሪፖርት ያቀርባል።
በአርቲፊሻልኢንተለጀንስ ፣በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ እና ዳታ ሳይንስ ዘርፎች ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተዘጋጀውን የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችል ነጻ የኦንላይን ሥልጠና ለመውሰድ በዚህ ሊንክ https://ethiocoders.et/ ላይ ይመዝገቡ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች