+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በአደዋ የተገኙ ድሎችን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በደመቀ ስነስርዓት ተከብሯል።

በዓሉ በአደዋ የተገኙ ድሎችን፣ የጀግንነትና የአንድነት ስሜቶችን በማፅናት ለተቋሙና ለሀገር ተልዕኮ ስኬት እንድንተጋ በዛን ዘመን ራሳችንን እንድናይ ብሎም የኢትዮጵያዉያን የወል ታሪክና ትርክት ማጠንጠኛ ዓርማ የሆነውን የአድዋ ድል ለትውልድ ለማስገንዘብና ለተጨማሪ የወል ድሎች ተነሳሽነት ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞቻችን ለሃገር ክብር ነጻነትና ሉዓላዊነት በአንድ አቋም ተሰልፈው፣ አንድነታቸውንና ህብረታቸውን አጠናክረው ሰፊ ተጋድሎ በማድረግ ጊዜ የማይሽረው በወርቅ የተፃፈ የሀገር ታሪክ አስረክበውናል ብለዋል፡፡

"አደዋ ከሁሉም በላይ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ የአደዋን ድል ያንን ጀግንነት ያንን ከሁሉም የላቀ ፋይዳ ያለው ደማቅ ታሪክ የተጻፈው አርበኞቻችን በተደላደለ ሁኔታ ሳይሆን በችግር ውስጥ ሆነው ለሀገራቸው ታሪክን በወርቅ የፃፉበትን ተጋድሎ ወደ ራሳችን በማምጣት በተሰማራንበት ሁሉ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

አድዋ ለኢትዮጵያውያን በተለይም ለዛሬው ወጣት ታሪክ ብቻ ሳይሆን አስገዳጅ ተልዕኮና አደራም ጭምር ነው ያሉት ሚኒስትሩ አርበኞቻችን በጀግንነት ታግለው ያቆዩልንን ሀገር በኢኮኖሚ እንድትበለፅግ ወጣቱ ከድህነት ጋር ተጋፍጦ ራሱንና ሀገሩን በመለውጥ የአፍሪካ ብሎም የአለም ተምሳሌት የምትሆንበትን እድል ሊፈጥር ይገባል ብለዋል፡፡

በዘመናዊው ዓለም የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ስም ተደጋግሞ ከሚነሳባቸው ክስተቶች መካከል አንዱ ለመሆን ከመብቃቱ ባሻገር በተለይ ደግሞ በጥቁሮች ዘንድ የዓድዋ ድል ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ መነቃቃትንና ተስፋን የሰጠ ክስተት መሆኑን አስገንዝበዋል።

አክለውም ሀገራችን እንዲሁም ተቋማችን እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ለማሳካት አንድ ሆነን በትብብርና በቅንጅት በመስራት ጉልህ የሆነ አሻራችንን ለማስቀመጥ መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በዓሉን መሰረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ የጋራ ውይይት የተካሄደ ሲሆን አድዋን ሁላችንም የወደቅንበት የሁላችንም የ ገዥ አሰባሳቢ ትርክት መፍጠሪያ የሆነ የጋራ ድላችንና ታሪካችንን በማክበር በተሰማራንበት ታሪክ ለማስመዝገብ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ ዝግጅቱ ለሁሉም ትልቅ አቅም እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ