+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ባሉ ቁልፍ የልማት ስራዎች ላይ 4ኛ ቀኑን የያዘው የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራ እየተካሄደ ነው ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር ከፍተኛ አመራሮች ሦስተኛ ቀን የአዲስ አበባ ከተማ የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራዎች በቦሌና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ ቁልፍ የልማት ስራዎችን ከስራ ሀላፊዎች ጋር በመወያየት የስራ ጉብኝት አካሂዷል።

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን ትልቅ ሚና ያለውን የግሉን ዘርፍ በመደገፍና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ለኢኮኖሚያችን እድገት ያለውን አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ስላልሰራንና አቅማችንን አሟጠን ስላልተጠቀምን እንጂ ኢትዮጵያ ሀገራችን ሰፊ የመልማት አቅም ያላት ሀብታም ሀገር ናት ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ በምሳሌነት የሚጠቀሱትን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በማስፋት ከውጪ የምናስገባውን ከማስቀረትም አልፎ የምንልክበት እና የውጪ ምንዛሪ የምናገኝበትን ስርዓት መፍጠር አለበት ብለዋል።

የፕላንና ልማት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ያየናቸው ስራዎች የወደፊት የእድገት ተስፋዎቻችን ስለሆኑ ሁላችንም አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ልናሰፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ግብርና ሁሉን የሚይዝ ህይወትን የተሸለ የሚያደርግ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ መንግስት የተቀናጀውን የከተማ የግብርና ልማትን በማጠናከር ወደ ግብርና ኢንዱስትሪ መቀየር የሚችልበትን አመላካች ውጤት ማየት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ጉብኝቱ የቦሌ ክፍለ ከተማ ያሉ አስገራሚ የጋርመንት ምርቶችን፣ በቡና ላይ እየተጨመሩ ያሉ እሴቶችን፣ በፈርኒቸር ስራ ላይ የተሰሩ ውጤቶችን፣ በትምህርት ቤት የተደረጉ ማስፋፊያዎች፣ የወጣቶች የስፖርት ማዕከሎችን፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርናንና የሌማት ቱርፋቶችን የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስኬታማ በሆነ መልኩ አጠናቋል፡፡

በመጨረሻም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመወያየት ስራዎችን ዲጂታል ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን በተቋሙ በመገኘት ጉብኝቱን የጀመረ ሲሆን በቀጣይ ቀናት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ