+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ስራዎች ላይ የሚካሄደው የሱፐርቪዥን ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር ክቡራን ሚኒስትሮች የሁለተኛ ቀን የአዲስ አበባ ከተማ የሱፐርቪዥን ድጋፍ ስራዎች የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮን እና በቦሌ ክፍለ ከተማ የተሰሩ ልዩልዩ የልማት ስራዎችን ከስራ ሀላፊዎች በመወያየት መሬት ላይ ያሉ ስራዎችን ቅኝት አድርገዋል፡፡

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ ያላትን የከተማ መሬት ሀብት ዲጂታላይዝ የማድረጉ ስራ ለማህበረሰባችን የስራ ቅልጥፍናን፣ አስተማማኝ አገልግሎትን፣ ምርታማነት፣ ግልፀኝነትንና እርካታን ስለሚፈጥር እየተሰሩ ያሉትን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ስራዎች አጠናክሮ ከማስቀጠል ውጪ አማራጭ እንደሌለ አንስተዋል፡፡

ሀገራችን ብዙ ሀብትና እምቅ የሆነ አቅም አላት ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በሱፐርቪዥን ድጋፍ እያየናቸው ያሉ ስራዎች አርኪ ቢሆኑም ለቀጣይ ትውልድ የተሻለችና የለማች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ቀጣይነት ያለው ድርብርብ ውጤቶች ለማምጣት ብዙ መትጋት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በተለይ የዲጂታል ክህሎት ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የተገኘውን የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠናን ዕድል ሁሉም የዘርፉ ተዋናዮች ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ስራዎችን ዲጂታላይዝ ስናደርግ ስልጣንን አሳልፈን ለሲስተም እንድንሰጥ ስለሚያደርግ ብልሹ አሰራሮችን አስወግዶ ፍትሀዊነትን ስለሚያሰፍን በኢኮኖሚ እድገታችን ላይ ያለው ሚና አቻ እንደማይኖረው አስረድተዋል፡፡

ሰው አካባቢውን ይቀይራል አካባቢ ደግሞ ሰውን ይቀይራል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ በተቋማት ዙሪያ የተፈጠሩ ሳቢና ምቹ አካባቢዎች ለመጣው ለውጥና ለተመዘገበው ውጤት ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

የሱፐርቪዥን ድጋፉ አዲስ አበባን አዲስ ከማድረግ አንጻር እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ስራዎችን፣ የሌማት ቱርፋቶችን፣ የአቅመ ደካሞች የምገባና የመኖሪያ ቤት፣ የወጣቶች የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የከተማ ግብርና፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የአገልግሎት ሰጭወች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ስራዎችን ዲጂታላይዝ ከማድረግና ተቋማትን አቀናጅቶ ከመምራት፣ ከስራ ፈጠራ እና ሌሎች ሪፎርሙ ያመጣቸው ለውጦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ