+251118132191
contact@mint.gov.et
በአፍሪካ አህጉር የላቀ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራን ማፍጠን እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኤክስቴንሲያ (Extensia ltd) ጋር በመተባበር ከየካቲት 19-20/2017 ዓ.ም የሚቆይ የአፍሪካ ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የሚመክረው የ2025 ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉባኤ (Accelerated Digital Transformation Summit 2025) በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉባኤው በአፍሪካ ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራን በማሳለጥ የላቀ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ያለመ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የፓን አፍሪካን የፖሊሲ አውጪዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች ፣ የዘርፉ ባለሞያዎች እና ባለሀብቶች ሁሉም ለአፍሪካ የዲጂታል ለውጥን ለማፋጠን በቅንጅት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የተግባር ጊዜ አሁን ነው ያሉት ሚኒስትሩ በመላው አህጉር፣ ዲጂታላይዜሽን ኢኮኖሚዎችን ለመገንባት፣ አዳዲስ እድሎችን በመክፈት እና አፍሪካ በአለም አቀፍ ገበያ ያላትን አቋም ለማሳደግ በትጋት መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል።
የዲጂታል አገልግሎቶች እና በአይሲቲ የሚመሩ ኢንዱስትሪዎች ያላቸውን አቅም ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ እምቅ አቅምን ለመገንዘብ እና ለሁሉን አቀፍ እድገት ለማምጣት ትብብርን፣ ፈጠራንና ቆራጥ እርምጃን እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል።
የኤክስቴንቲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ Mr. Tariq Malik ለአህጉሪቱ የተፋጠነ የዲጂታል እድገት አዳዲስ እድሎችን በማጉላት፣ በቁልፍ ውሳኔ ሰጪዎች፣ በዘርፉ መሪዎች እና ባለሀብቶች መካከል ትብብርንና ትስስርን በማጎልበት ብሎም ፈጠራን በማስፋፋት ጉባኤው ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራን በማሳለጥ የአፍሪካን የወደፊት ዲጂታል ኢኮኖሚን በቅንጅትና በትብብር በመገንባት የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራ በጉባዔው ላይ ተገልጿል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ኤክስቴንሲያ በአፍሪካ ከመንግስት እና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ መሪዎች፣ ውሳኔ ሰጪዎች እና የዘርፉ መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ አገልግሎት ሰጪዎች እና የአይሲቲ ዋና ዋና ተጠቃሚዎችን ጨምሮ ከ300 በላይ ሰዎች በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች