+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በአፍሪካ ኢጋድ አገሮች ውስጥ የኢንተርኔት መሠረተ ልማትና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ለማጠናከር የሚያስችል የ2025 የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከበይነመረብ ማህበረሰብ (Internet Society) እና ከዊንጉ አፍሪካ ( Wingu Africa ) ጋር በመተባበር በአፍሪካ ኢጋድ አገሮች የኢንተርኔት ስነ-ምህዳር መሰረት ለመጣል የሚያስችል ለ3 ቀን የሚቆይ የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ (አይዲሲ) 2025 በአፍሪካ ኢጋድ አገሮች ውስጥ የኢንተርኔት መሠረተ ልማትና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ለማጠናከር ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ ሁሉንም ዜጎች የሚያጎለብት እና ሀገራችንን በአፍሪካ ዲጂታል አብዮት ግንባር ቀደም እንድትሆን የሚያስችል ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ዝግጅት በኢትዮጵያ እና በሰፊው የኢጋድ ቀጠና ያለውን ዲጂታል መልክዓ ምድር ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂያችን በመመራት የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስደናቂ እድገት እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዞ የወደፊት ህይወታችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ለሳይበር ደህንነት፣ ለዳታ ጥበቃ እና ለዲጂታል እውቀት ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የቴሌኮም መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ አመርቂ ምእራፎችን መከናወናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ የ4ጂ ሽፋኑን ወደ 34.8% መድረሱ፣ የ5ጂ አገልግሎት በ14 ከተሞች መጀመሩ የሞባይል ደንበኞች ቁጥር 80.5 ሚሊዮን መድረስ፣ የሞባይል ብሮድባንድ ተጠቃሚዎች 45 ሚሊዮን ማለፉ በሀገር ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የመጡ ለውጦች ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

ከዲጂታል መተግበሪያዎች አንጻር ቴሌቢር ከ51.54 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚ ማፍራቱ የዲጂታል ፈጠራ ፋይናንሺያል ማካተትን ለመምራት እና ኢትዮጵያውያን ግብይቶችን ለመለወጥ ያለውን ኃይል ያሳያል ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ እንደ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲ ያሉ አገሮችን የሚያጠቃልለው ጠንካራ፣ ይበልጥ የተቀናጀ የኢንተርኔት ስነ-ምህዳር መሰረት ይጥላል ብለዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የመንግስት ተነሳሽነት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት - የግሉ ሴክተር ፣ ሲቪል ማህበረሰብ ፣ አካዳሚዎች እና ዓለም አቀፍ አጋሮች - ይህንን ራዕይ ለመቅረፅ እና እውነተኛ ሁሉን አቀፍ እና የበለፀገ አሃዛዊ የወደፊት ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲተባበሩ ጥሪ ተላልፏል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ