+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በኢትዮጵያና በእስራኤል ትብብር የተዘጋጀ የሳይበር ደህንነት አውደ ጥናት ተካሄደ

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በእስራኤል ኤምባሲ ትብብር የተዘጋጀው "የሳይበር ደህንነት አዝማሚያዎች እና እድገቶች" ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ፣ "የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ራዕይን ለማሳካት በሳይበር ደህንነት ላይ ሰፊ ልምድና ትልቅ አቅም ካላት እስራኤል ጋር በትብብር መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ትብብር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዲጂታላይዜሽን ከማፋጠኑም ባለፈ፣ ለውጭ ኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ እንዲሁም የፋይናንስና ስልታዊ መሠረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃት የሚከላከል አስተማማኝ የዲጂታል ከባቢ አየር ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከልና ጠንካራ የቴክኖሎጂ መሰረት ለመገንባት ራስን ማብቃትና ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች መማር አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭራሃም ንጉሴ፣ የሳይበር ደህንነት የሀገር ደህንነት እና የኢኮኖሚ ጥንካሬ መሰረት መሆኑን በመጥቀስ፤ ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞዋ የዲጂታል ንብረቶቿን መጠበቅ እንዳለባት አሳስበዋል።

እስራኤል ባለፉት ሁለት ዓመታት የገጠሟትን የጸጥታ ፈተናዎች ተከትሎ፣ የሳይበር ምህዳሩን እንደ ትልቅ የጦር ግንባር በመመልከት በመንግስትና በግል ዘርፍ የመከላከል አቅሟን ማጠናከሯን አምባሳደሩ ገልጸዋል።

የእስራኤል የሳይበር ደህንነት ስኬት በብቁ የሰው ኃይል፣ በተቋማት ትብብርና በፈጠራ ባህል ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህን ተሞክሮ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ለመተግበር ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

አውደ ጥናቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ በማሸጋገር ረገድ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍትና የኢትዮጵያን ዲጂታል የወደፊት እጣ ፈንታ አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚረዳ ተመልክቷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ