+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ታንዛንያን የ2025 አስተናጋጅ ሀገር በማድረግ ተጠናቀቀ፡፡

ከህዳር 11 እስከ ህዳር 13 “Building our Multistakeholder Digital Future” በሚል መሪቃል በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተጠናቋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባዘጋጁትጉባኤ የሳይበር ደህንነትና ወንጀል፣ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ፣ የኢንተርኔት አስተዳደር፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የዲጂታል ሰብአዊ መብቶች፣ በዘርፉ ሁለንተናዊ የተደራጀ አህጉራዊ ግኑኝነትን መፍጠር እና ሌሎች አጀንዳዎች ተዳሰውበታል።

በፎረሙ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የአፍሪካ ዲጂታል ጉዞን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ መንግስታት፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች እንዲሁም አለም አቀፍ አጋሮች በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተለይም በተመጣጣኝ ዋጋ ዘላቂ የብሮድባንድ መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስትመንቶችን እንዲያጠናክሩ የሚያስችሉ ፓሊሲዎችን ተግባራዊ በማድረግ አፍሪካውያንን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

የዲጂታል አገልግሎቶችን ከሳይበር አደጋዎች የሚከላከሉ ስራዎች መጠናከር አለባቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በዲጂታል መድረኮች ላይ የዜጎችን እምነት ለመፍጠር ከግሉ ሴክተር እና ከትምህርት ተቋማት ጋር መሰራት እንዳለበት አንስተዋል።

አያይዘውም በመላው አፍሪካ ያሉ መንግስታት ፈጠራንና ውድድርን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ የዜጎችን መብት የሚያስጠብቁ ስራዎችን በትኩረት እና በትብብር መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

ከአፍሪካ ውጭ ያሉ ተጋባዥ ሃገራትን ጨምሮ 68 ሀገራት የተሳተፉበት ይህ አህጉራዊ ጉባኤ በቀጣይ በሳዉዲ ለሚካሄደው የአለም ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ እንደ አፍሪካ የሚወሰዱ አጀንዳዎች ተለይተውበታል ተብሏል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሲካሃደ የቆየው 13ተኛ የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በ2025 የሚካሄደውን 14ተኛው የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ታንዛንያ እንድታስተናግድ ውስኔ በማሳለፍ ተጠናቋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ