+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በኢትዮጵያ እየተሰራ ባለው ምቹ የስታርታፕ ስነምህዳር ግንባታ ወጣቶች ከዘርፉ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ጋር በጋራ ለስድስት ወራት ያሰለጠናቸውን ለ12 ስታርታፖች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል።

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ሀገራችን ያላትን ከፍተኛ ወጣት ሀይል በዘርፉ ላይ በማሰማራት ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤቶችን አምርቶ የሀብት ባለቤት ከመሆንም አልፎ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚቻልበትን ሰፊ እድል ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

መንግስት ከለውጡ በኃላ ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት፣ ከስታርታፕ ስነምህዳር ገንቢዎች እና ከውጪ አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር በዘርፉ ላይ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የቴክኖሎጂ ፍላጎቱ ብዙ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት በአጭር ጊዜ ለማምጣትና ዘላቂና ተሻጋሪ የሆነ ልማት ለማጎልበት ዘርፉ ወሳኝ ሚና ስላለው ከራሳችን አልፈን ለአፍሪካና ለሌሎች የአለም ሀገራት መትረፍ እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።

የኮርያ ዓለም አቀፍ ትብብር አስተባባሪና ኤክስፐርት ቾይ ያንግ ጁን (ዶ/ር) በበኩላቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ በዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ የፕሮጀክት አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሁለት ስታርታፖች የ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ