+251118132191
contact@mint.gov.et
በኢትዮጵያ ወደ ገበያ የገቡ ስታርታፖች በዩናይትድ አረብ ኤሜሬት በየአመቱ የአንድ ሚልዮን ዶላር በሚያሸልመው የዛይድ ዘላቂነት ሽልማት ውድድር ላይ ሊሳተፉ እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ወደ ገበያ የገቡ ስታርታፖች የሚወዳደሩበት የአንድ ሚልዮን ዶላር የሚያሸልመው በዩናይትድ አረብ ኤሜሬት የሚገኘውን የዛይድ ዘላቂነት ሽልማት (Zayed Sustainability Prize) ድርጅት ላይ ለአሸናፊነት እንዲሳተፉ ለማገዝ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከድርጅቱ የስራ ሀላፊዎች ጋር መከሩ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን መንግስት በፈጠረው ምቹ የስታርታፕ ስነ-ምህዳር በመጠቀም ሀብት ከማፍራት አልፈው የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የስታርታፕ ውጤቶች ተፈጥረው በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን መቻላቸውን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ብዙ መፍጠር የሚችል ወጣት ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሩ የተወዳዳሪነት ስሜትን ያዳበረ በዓለም አቀፍ እውቅናንና ተፅኖ መፍጠር የሚችል ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቀ ወጣት ለማፍራት ኢትዮጵያ ተግታ እየሰራች ነው ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኒሼቲቪ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች (UAE) የተገኘው የ5 ሚልዮን ኮደርስ ስልጠና ያስገኛቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታና ለተደረገው ድጋፍ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መንግስትን በማመስገን በሚደረጉ የሁለትዮሽ የትብብር ስራ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ አመላክተዋል።
የዛይድ ዘላቂነት ሽልማት (Zayed Sustainability Prize ) ድርጅት ባለቤት ሚስተር ሞሃመድ አል ፋርዳን የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የሁለትዮሽ ትብብር ለግል አልሚዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው ድርጅቱ በኢትዮጵያ ሶላር ኤነርጅ ልማት ዘርፍ ላይ እንደተሰማራ ጠቁመዋል።
አክለውም ኢትዮጵያውያን ስታርታፖች ለውድድር ሽልማቱ ብቁ እንዲሆኑ ስልጠና በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
ምክክሩን በቀጣይ በማጠናከር ለውድድር ብቁ የሆኑ ስታርታፖችን በመለየት በሁለትዮሽ የትብብር መርሃ ግብር ላይ ለመስራት ተስማምተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች