+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በኢትዮጵያ የማስተማሪያ ሆስፒታሎች ውስጥ ተጨማሪ አዳዲስ የካንሰር ህክምና ማዕከላት እንዲቋቋሙ ጥሪ ቀረበ።

የኢፌዲሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሁዋ ሊዩ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በኦስትሪያ ቬና እየተካሄደ ባለው የቴክኒክ ትብብር ፕሮግራም የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የዘርፉ ስራዎችን ያቀረቡ ሲሆን ጎን ለጎን ከአለማቀፍ ተቋማት አመራሮች ጋር የተናጥል ውይይት አደረገዋል።

ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሁዋ ሊዩ ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ የማስተማሪያ ሆስፒታሎች ውስጥ ተጨማሪ አዳዲስ የካንሰር ህክምና ማዕከላት እንዲቋቋሙ በመጠየቅ መንግስት ለጀመረው ጥረት የኤጄንሲው የተለመደ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከልን ለማቋቋም የተጀመረውን ስራ በማገዝ ረገድ የቴክኒክ፣ የፋይናንስ እና የሰው ሃይል ልማት ውጥኖችን በማካተት የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ በIAEA Atoms 4 Food ኢኒሸቲቭ ላይ ለመተባበርና ኢትዮጵያ የዚሁ ተጠቃሚ እንድትሆን ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን ለይተው ጥያቄ እንደሚቀርብም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በእንስሳት ጤና ላይ ያተኮረ አህጉራዊ ማዕከል (ዲ.አር.ሲ.) ማቋቋም፣ ከብሔራዊ የእንስሳት ህክምና ተቋም፣ ከብሔራዊ ጸጸ ዝንብ ማጥፊያ ማዕከል እና የአፍሪካ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርመራ ማዕከልን በማቀናጀት ለታሰበው (Regional Designated Center) ላይ ያተኮረ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ይህም ተቀባይነት በማግኘት ወደ ስራ እንደሚገባ ታምኖበታል።

በውይይቱ ላይ ሚስተር ሁዋ ሊዩ የኤጀንሲውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ ቻይና እና IAEA በተለያዩ የጋራ ተጠቃሚነት ውጥኖች ላይ ለመፈራረምና ለመስራት የተዘጋጀውን እና ለአፍሪካ ህብረት የተላከውን የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ለማፋጠን የሚኒስትሩን ድጋፍ ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ በነዚህ ኤጀንሲዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያን እና አፍሪካውያን በቴክኒክ እና አስተዳደራዊ ቦታዎች ላይ እንዲሳተፉ እና እንዲቀጠሩ ሊታሰብበት እንደሚገባ ያነሱ ሲሆን በሃላፊዎቹ በኩልም ውይይት ተደርጎበት ወደ ተግባር እንደሚገባም ተገልጿል።

እየተካሄደ በሚገኘው ፕሮግራም ላይ በተደረጉ የፓናል ውይይት ላይ ሚኒስትሩ በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ከአለማቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በተለያዩ ዘርፎች የተደረጉላትን ድጋፎች አንስተው ያመሰገኑ ሲሆን በቀጣይ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሀገራቸውን ቀዳሚ የልማት እቅዶች (national priorities) አስረድተዋል።

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ