+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በምርምር ስራዎች ላይ ያለውን ሚና ለማጠናከርና በሥነ-ምግባር የታነጸ አጠቃቀምን ለማስፈን የሚያስችል የበይነ-መረብ ስልጠና ተካሄደ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር "የምርምር ሥነ-ምግባር በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘመን" በሚል መሪ ቃል፣ ከ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ጋር የተገናኘ ሀገራዊ የቨርቹዋል ሥልጠና መርሃ ግብር አካሂዷል።

የሥልጠናውን የመክፈቻ ንግግር በበይነ መረብ ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በምርምር ሂደት ውስጥ ሰፊ ዕድሎችን እየፈጠረ ቢሆንም፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ ውስብስብ የሥነ-ምግባር ፈተናዎችንም ይዞ መምጣቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ኃላፊነት የሚሰማውና ተጠያቂነት ያለው የፈጠራ ሥርዓት ለመዘርጋት ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ለዚህም የስታርታፕ አዋጅ (Startup Proclamation) እና የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ በዋቢነት የሚጠቀሱ የሕግ ማዕቀፎች መሆናቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሀገሪቱ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕቀፍን ለማጠናከርና የብሔራዊ የምርምር ፋውንዴሽንን ለማቋቋም የምታደርገው ጥረት፣ ሳይንሳዊ ግኝቶች ከሀገራዊ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙና ሥነ-ምግባራዊ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

በምርምር ዘርፍ እንደ ግልጽነት፣ አድልዎ ቅነሳ፣ የመረጃ ጥበቃና የሰዎች ቁጥጥር ያሉ ጉዳዮች አማራጭ ሳይሆኑ መሠረታዊ አስፈላጊነቶች መሆናቸው በሥልጠናው ላይ ተመልክቷል። ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምን ማድረግ ይችላል ከሚለው ባለፈ፣ ምን ማድረግ አለበት በሚለው የሞራል ጥያቄ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ፍትሃዊነትን ያከበረ አጠቃቀም ሊኖር እንደሚገባ ገልፀዋል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሥነ-ምግባራዊ ምርምር የሚካሄድበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት የገለጹት መሪ ስራ አስፈፃሚ ተሳታፊዎች ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ ለበለጠ ሀገራዊ ጥቅም እንዲያውሉት ጥሪ አቅርበዋል።

ሥልጠናው ተመራማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ምርምር ሲያካሂዱ የሚያጋጥሟቸውን የስነ-ምግባር ተግዳሮቶች እንዲረዱና የምርምር ታማኝነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራዊ አቀራረቦችን እንዲላበሱ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ