+251118132191
contact@mint.gov.et
በኢትዮጵያ የተዘጋጀው የተለያዩ ሀገራትን ያሳተፈው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ ንቃት የተሞላበትና ብዙ የቴክኖሎጂ እውቀቶች ልምድ የተጋሩበት እንደነበረ ዶ/ር ፎዚያ አሚን ገለፁ፡፡
ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም ሲካሄድ የቆየው ከ14 ሀገራት በላይ የተሳተፉበት 41 ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበት ታላቅ አለም አቀፍ ዓውደ ርዕይ በሀካቶን ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት ተጠናቋል፡፡
በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፎዚያ አሚን ኢትዮጵያ የደቡብ ትብብር አባል ሀገራትን ያሳተፈ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ በዘርፉ ላይ ለተሰማሩት የቴክኖሎጂ ተዋናዮች ትልቅ አቅም መፍጠሩን ገልፀዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ልማት የተናጠል ስራ አይደለም ያሉት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አባል ሀገራቱ ዘርፉን ለማሳደግ የፈጠሩት ምቹ የትብብር ስነምህዳር ለሁሉም ሀገራት ከስራ ፈጠራና ከቴክኖሎጂ ማበልፀግ ባሻገር የትብብርና የኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል ብለዋል፡፡
እንዲህ ያሉ ዓውደ ርዕዮች ተጠናክረውና ተናበው በሄዱ ቁጥር አባል ሀገራቱ የቴክኖሎጂ አብዮት ፈጣሪዎችና ተጠቃሚዎች መሆን እንደሚችሉ ካየናቸው ውጤቶች ማረጋገጥ እንደሚቻል አንስተዋል፡፡
የደቡባዊ ትብብር ድርጅት (OSC) ዋና ጸሃፊው መንሱር ቢን ሙሳላም በትምህርትና ክህሎት፣ በፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ በዘላቂ ትራንስፖርት፣ በንጹህና ተመጣጣኝ ኃይል፣ በዘላቂ ግብርና እና በተቀናጀ ጤና አገልግሎት ዘርፍ ላይ የተካሄደው ዓውደ ርዕይ ላይ የተፈጠረው የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግርና የነበረው ሁነት ሰኬታማ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የተካሄደው ዓውደ ርዕይ በሁለት አመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ በመሆኑ በጋራና በትብብር የምንሰራቸው ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁሉም የቴክኖሎጂ ተዋናዮች የመፍጠር አቅማቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
በደቡብ ትብብር ድርጅት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ዓውደ ርዕዩን በትብብር አባል ሀገራቱ የተገኙ የቴክኖሎጂ እውቀቶችን በማጋራት በቀጣይ አብሮ መስራት የሚቻልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የታለመለትን አላማ አሳክቷል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የሀካቶን ወድድር አሸናፊዎች ሽልማት በመስጠት የመዝጊያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች