+251118132191
contact@mint.gov.et
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ ልማትን የሚያፋጥን የምርምርና ኢኖቬሽን ክላስተር የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ቴክኖሎጂ የምታደርገውን ሽግግር በላቀ የሳይንስና ምርምር ድጋፍ ለመምራት ያለመ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የዘርፉን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የመኪና ባትሪዎችን የመጠገንና አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ በአግባቡ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል (Recycling) የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በሀገር ውስጥ መገንባት ወሳኝ መሆኑ ገልፀዋል።
ነባር የነዳጅ መኪናዎችን ወደ ኤሌክትሪክ መኪናነት የመቀየር (Retrofitting) ቴክኖሎጂን ማስተዋወቅና ማስፋፋት አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ወደ አረንጓዴ ኢነርጂ ለመቀየር ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በዝርዝር አስገንዝበዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን፣ የቴክኖሎጂው ባለቤትና አመንጪ ለመሆን ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተክለማርያም ተሰማ ኢትዮጵያ ከነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣትና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የጀመረችውን ጉዞ ለማሳካት የቴክኖሎጂ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።
መኪናዎችን ለመንዳት፣ ለመመርመርና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ አጋዥ ሶፍትዌሮችን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የማበልጸግ አስፈላጊነት የቴክኖሎጂ ነፃነትን ለማረጋገጥ አንዱ ቁልፍ ነጥብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የመንግሥትና የግል ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የህግ ማዕቀፎችን በማጠናከርና የሰው ኃይልን በማሰልጠን እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ለተግባራዊ ስራ መነሻ የሚሆን የትብብር ሰነድ እንዲያዘጋጅ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች