+251118132191
contact@mint.gov.et
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራው ልዑካን ቡድን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጎበኘ።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራው ልዑካን ቡድን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የፍትህ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን ተዟዙረው በመጎብኘት በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
የጉብኝቱ አላማ የፍትህ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በማዘመንና ዲጂታላይዝ በማድረግ ከተቋሙ ጋር በጋራ በመስራት ጊዜውን የሚዋጅ አገልግሎት የሚሰጥበትን ስርዓት ለመፍጠር ያለመ ነው።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን ያሉ ተቋማት አለም የደረሰበት የዲጂታል ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ለተገልጋይ ዘመናዊ አገልግሎትን በመስጠት የኢትዮጵያን እድገት ከፍ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ጊዜው የሚጠይቀውን የዲጂታል አለም መጠቀም ፍላጎት ሳይሆን ግዴታ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በተለች የፍትህ ስርአቱ የተገልጋዩን እርካታ እንዲጨምር ፈጣንና ግልጽ ፍትህ ተደራሽ እኖዲሆን ማረጋገጥ ከሀገር ሰላምና ልማት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው በመሆኑ በሙሉ ወደ ዲጂታል አሠራር መግባት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የዳኝነቱን ስርዓት ዲጂታላይዝ በማድረግም ለህዝባችን የሚሰጥ አገልግሎት የተቀላጠፈና ፍትህዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በጋራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ሀገራዊ ስራዎቻችንን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሀብት፣ የጉልበትና የጊዜ ብክነትን በማስቀረት ግልፅና ለሁሉም ተደራሽ የሚሆን ፍትህን ለማስፈን እየሰራን ነው ብለዋል።
ክቡር ፕሬዚዳንቱም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተደረገልን ያለው ድጋፍ ትልቅ አቅም ፈጥሮልናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀት ለመታጠቅ በሰው ሀብት ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም ገልፀዋል።
የፍትህ ስርዓቱን ለማዘመን በማያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ በምክክሩ ላይ ተጠቁሟል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች