+251118132191
contact@mint.gov.et
በኢኖቬሽን የተመራ ሀገራዊ ኢኮኖሚ ለመገንባት ምርምሩ ከዩኒቨርስቲ፣ ከኢንዱስትሪውና ከግል ዘርፉ ጋር ትስስሩ መጠናከር አለበት ብለዋል ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢንዱስትሪ፣ ከዩኒቨርስቲ፣ ከምርምር ተቋማት እና ከክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለመፍጠር ኢንዱስትሪውን ከምርምር ዘርፍ ጋራ ለማስተሳሰርና ለማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ምክክሩ ሀገራዊ ምርምሩን ከዩኒቨርስቲ፣ ከኢንዱስትሪውና ከግል ዘርፉ ጋር በማስተሳሰር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሀብት ባለቤትና በእውቀት የዳበረ መፍጠር፣ ማምረትና መጠቀም የሚችል የሰው ሀይል ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ሀገራዊ የምርምርና የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በማስተሳሰር አዳዲስ ውጤቶችን በማውጣት የማህበረሰባችንን ችግር ለመቅረፍ ከውጪ የምናስገባውን በራሳችን አቅም አምርተን ለመተካት የሚያስችል ስርዓት መገንባት የህልውና ጉዳይና አስገዳጅ መሆኑን ገልፀዋል።
ብዙ ያደጉ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ጠንካራ የሆኑ ሀገራት መነሻቸው ምርምር ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በምርምር ልማት ላይ መንግስትና የግሉ ዘርፍ በጋራ ኢንቨስት በማድረግ እያንዳንዱ ኢንዱስትሪ የራሱ የምርምር ማዕከል ኖሮት የምርቱን ጥራት በመለካት ጥራቱን እየጨመረ ማደግ አለበት ብላዋል፡፡
የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ እንደ ሀገር መንግስት የምርምር ዘርፉን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ለማዋል ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ዘርፉ ለሀገር እድገት እንዲውል ከተፈለገ ሀሉም የዘርፉ ላይ ያሉ ተዋናዮችና ተቋማት በመናበብና በቅንጅት ላይ የተመሰረቱ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ምርምር በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የምርምር፣ የኢንዱስትሪና የዩኒቨርስቲ ትስስር ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡
የምክክር መድረኩ ላይ ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በቀጣይ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ግንኙነቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች