+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ የምርምር ተቋማት የሚደረጉት ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ምቹ ስነምህዳር እየፈጠርን እንገኛለን ። ዶ/ር ባይሳ በዳዳ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ተመራማሪዎች ለሦስት ተከታታ ቀናት በአካልና በኦንላይን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስልጠናው በምርምር ፕሮጀክት አፃፃፍ ዘዴ፣ በምርምር ስታቲስቲካዊ ስሌት፣ R and Python programing እና ሌሎች የምርምር ሙያን የሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ሲሆን በሀገራችን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት በምርምር ስራ ለተሰማሩ ተማራማሪዎች አቅምን ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡

በስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ጉዞ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በዩኒቨርስቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በኢንዱስትሪዎች የሚደረጉ የምርምር ስራዎች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በመግለፅ የሚሰሩ ችግር ፈቺ ምርምሮች ውጤታማ ለማድረግ ምቹ ስነምህዳር እየፈጠርን እንገኛለን ብለዋል።

ለችግር ፈቺ ምርምሮች፣ ለዲጂታል አይ ሲ ቲ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለፈጠራ ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደ ሀገር ለተያዙ የልማት ዕቅዶች ስኬታማነት የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴታው ሚኒስቴር መስሪያቤታቸው በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና የምርምር ተቋማት የሚደረጉት የምርምር ስራዎች የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት መሳለጥ ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይልና ችግር ፈቺ ምርምሮችን ወሳኝ እንደሆኑና መንግስት የጀመረውን የ5 ሚልየን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢንሼቲቭ ስልጠና ለምናካሂደው የምርምር ስራዎች ትልቅ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በመግለፅ ተመራማሪዎች ስልጠናውን እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡

የ5 ሚልየን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢንሼቲቭ ስልጠናን በዚህ ሊንክ፡-https://ethiocoders.et/ 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ