+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ ስልጠና እንቅስቃሴ ያለበት ደረጃ ተገመገመ።

የፌደራል ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ድጋፍና ክትትል ቡድን በክልሉ ያለውን “የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" ስልጠና አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት አረብ ኢሜሬት ጋር በመተባበር ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የዲጂታል እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ ታስቦ የተጀመረው ስልጠና በክልሉ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው በግምገማው ወቅት የተገለጸው።

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ምትኩ አስፋው እንደገለጹት በሚቀጥሉት 3 ዓመታት በክልሉ 150ሺህ ዜጎችን በማሰልጠንና ሰርተፊኬት እንዲያገኙ በማድረግ ሀብትና ስራ ፈጠራ ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በዚህም በክልሉ ያሉ የተለያዩ የስልጠና ማዕከላትን በማቀናጀትና ቁሳቁስ በማሟላት ዜጎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ይሁን እንጂ በአንዳንድ የክልሉ አከባቢዎች የኢንተርኔትና የሀይል መቆራረጥ ተግባሩን በተፈለገው ልክ ለማሳለጥ ማነቆ እንደሆነ አንስተዋል።

በክልሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር እያደገ መምጣቱን የጠቆሙት ኃላፊው በዚህም ስልጠናውን ለመከታተል የሚመዘገቡ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጀምሮ በየደረጃው ያለው አመራሮች ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ መጎልበት እያሳዩት ያለው ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት የሚበረታታ መሆኑን የተናገሩት የክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ መሳይ ኃ/ማርያም በክልሉ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞን እውን ለማድረግ የተጀመረው ጅምር አንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ገልጸዋል።

የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል እውቀትና ክህሎት በማሳደግ ዜጎች በዚህ ተለዋዋጭ አለም ተወዳዳሪና ብቁ ሆነው ስራ እንዲፈጥሩ እና ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ እንደሚያስችል የጠቆሙት አቶ መሳይ ዜጎች ሰልጥነው ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ ከመፈጠር ጀምሮ በክልሉ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በመድረኩ የተገኙት የባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በክልሉ ያሉ የስልጠና ማዕከላትን እና የባለሙያዎች ልየታ በማድረግና በማደራጀት ዜጎች እንዲሰልጥኑ በቅንጅት በሰሯቸው ዝርዝር ተግባራት ላይ ሀሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በክልሉ በተጀመረው የዲጂታላይዘሽን ሽግግር ላይ በአመለካከት፣ በክህሎትና በቴሌኮሚኒኬሽን መሠረተ ልማት እና ቁሳቁስ ረገድ የሚስተዋሉ ማነቆዎችንም እንዲሁ።

የዲጂታል እውቀት፥ ሀብት ለመፍጠርና ከመንግሥት ለዜጎች የሚሰጠውን እንዲሁም በግሉ ዘርፍ የሚቀርበውን አግልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ጊዜና ገንዘብ የሚቆጥብ በመሆኑ ተግባሩን በጋራ ትብብር አጠናከረው እንደሚቀጥሉም ነው የባለድርሻ አካላት የገለጹት።

የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችለውን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ በዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ