+251118132191
contact@mint.gov.et
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በወሳኝ ዘርፎች ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሰረት የጣለ ስራ ተሰርቷል።ዶ/ር በለጠ ሞላ
በክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የተዘጋጀው 3ኛው የዕውቀት ጉባዔ ተካሂዷል፡፡
ጉባኤው “የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራዎችን በመጠቀም ለፋይናንስ ዘርፉ አዳዲስ ገበያዎችን እና ማሳያዎችን መክፈት” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ነው።
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንደሃገር በአዳዲስ ፈጠራዎችና ቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስትመንታችንን በማጠናከር፣ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት የሀገር ውስጥ ስራ ፈጣሪነትን የሚያበረታታ ስነ-ምህዳር ለማጎልበት የሚያስችሉ የአሰራር ስርአቶች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን አንስተዋል።
በተለይም በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ መነቃቃትን የፈጠረውና ባለፉት አመታት ሲተገበር በቆየው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በወሳኝ ዘርፎች ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሰረት የጣለ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
ስትራቴጂው የአገር ውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሀገር ውስጥ መፍትሄዎችን መጠቀምን አበረታቷል ያሉት ሚኒስትሩ መጪው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም በዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶችን በማጠናከር የሚጠበቀውን ሃገራዊ ለውጥ ለማስመዝገብ ይረዳል ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ በኢትዮጵያ የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ኃላፊ መፍትሄ ታደሰ እንደገለጹት የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓትን ማሳደግ እና መደገፍ ወጣቶችን ለማብቃትና ፈጠራን ለማበረታታት ብሎም በዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ውጤታማ ስራ ለመስራት ያግዛል ብለዋል፡፡
የክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙኒር ዱሪ ኢትዮጵያ እያሻሻለቻቸው የሚገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎች ለዲጂታል ፋይናንስ ዕድገት ትልቅ በር የከፈቱ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን በተለይም
መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት አዳዲስ ገበያዎችን ና ፍላጎትን የሚያግዙ የአሰራር ስርአቶችን፣ፖሊሲዎችንና አቅጣጫዎችን በመዘርጋት ለዘርፉ እድገት በር መክፈት መቻሉ አንስተዋል።
በዝግጅቱ በተካሄደው የውይይት መድረኩ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በገበያ ፈጣሪዎች በተለይም ለጥቃቅንና አነስተኛ፣ ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ለአነስተኛ አርሶ አደሮች አዳዲስ ዕድሎችን እንዴት መክፈት እንደሚችሉ ተዳሷል።
በዚህም በMSMEs እና በአግሪ ፋይናንሲንግ ላይ በማተኮር ለፋይናንሺያል ኢንዱስትሪ አዳዲስ ገበያዎችን እና ሞዴሎችን ለመክፈት AI ፈጠራዎችን መጠቀም የሚኖረው ውጤታማነት ዙርያ የተገኙ ልምዶች ቀርበዋል።
በተለይም በ AI የታገዘ የብድር ውጤት አሰጣጥ ስርዓቶች፣ አማራጭ መረጃዎች እና አካታች፣ጥቅማ ጥቅሞችን ላላገኙ ስራ ፈጣሪዎች እና አነስተኛ ገበሬዎች የብድር ሞዴሎች ማመቻቸትን፤ሁሉን አቀፍ የብድር መሠረተ ልማትን ማስፋፋት እንዲሁም በአፍሪካ የሚመራ AI መፍትሄዎችን መውሰድ ላይ ያተኮሩ ሃሳቦች በውይይቱ ተነስተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች