+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት ውስጥ የሴቶች እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስነ-ምህዳር መፈጠር እንዳለበት ተገለፀ።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት፣ በ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ዋና ዋና ምሶሶዎችና አካታችነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።

መድረኩ የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂን በማስገንዘብ፣ የሴቶችን እምቅ አቅም በማጎልበትና ተሳትፏቸውን በማረጋገጥ የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግርና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማሳካት ያለመ ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ፣ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ሀገራችንን የሚያሸጋግርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለንን ተሳትፎ የሚወስን ትልቅ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን ሁሉም ዜጋ ሊገነዘብ እንደሚገባ አመልክተዋል።

እንደ ሀገር፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንባታ ሁሉን ያካተተና ተደራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ፣ በዘርፉ በቂ ዕውቀት ያለውና ቴክኖሎጂውን በተግባር መጠቀም የሚችል ዜጋ ማፍራት ይጠበቃል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ ቴክኖሎጂ ጊዜና ገንዘብ የሚቆጥብ፣ የስራ ክንውንና ምርታማነት የሚያሳድግ፣ ግልጽነትን የሚፈጥርና የሀገርና የግለሰቦች አቅም አጠቃቀምን የሚያሻሽል የዘመናዊ ዕድገት መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ለማፋጠንና ዘላቂ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶች ንቁ ተሳትፎና አመራር የማይተካ ሚና አለው።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ራዕይ በሴት አመራሮችና በፖሊሲ አውጪዎች ዘንድ በቂ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ፣ አካታችና ውጤታማ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ አዲስ መነሳሳት መፍጠሩ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ