+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በዲጂታል ዓለም ውስጥ ባንኮች ተወዳዳሪ ሆነው ለመውጣት የዲጂታል አስራሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ። 

ቴምኖስ ያዘጋጀውና በዲጂታል ባንኪንግ ላይ ያተኮረ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። 
በመድረኩ የተለያዩ የኢትጵያ ባንኮች በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ ያላቸውን የስራ እንቅስቃሴ አቅርበዋል። 
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ)  በዲጂታል ዓለም ውስጥ ባንኮች ተወዳዳሪ ሆነው ለመውጣት የዲጂታል አስራሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ተናገረዋል። 
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ላይ የዲጂታል ክፍያ አንዱ ምሰሶ ተደርጎ መቀመጡን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ባንኮች የደንበኞቻቸውን ፍላጎት ለማርካት ባንኮች ከአካውንት ማስተዳደር እስከ ደህንነት ጥበቃ ድረስ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዝርጋታ ላይ ማተኮር እንደሚገባችው አብራርተዋል። 
የቴምኖስ መካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሊ አልኮርን በባንክ ኢንደስትሪ ውስጥ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት የመኖርና ያለመኖር  ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። 
ከዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የመረጃ መረብ ደህንነት አንዱ ስጋት በመሆኑ የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባልም ተብሏል። 
መሰረተ ልማት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት እና የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ ያሉ ክፍተቶች ላይም ውይይት ተደርጓል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ