+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በዲጂታል ዓለም ውስጥ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ

ኢትዮ ቴሌኮምና ጂ ኤስ ኤም ኤ በጋራ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ላይ ያተኮረ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመደረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሀብታምና በድሃ እንዲሁም በከተማና በገጠር ያለ ልዩነት ሁሉን ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ ዙሪያ ኢትዮጵያ መሰረታዊ ለውጦችን እያደረገች መሆኑን ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው የዲጅታል ልዩነትን (digital divide) በመፍታት የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑንም ተናገረዋል።

የዲጂታል አሰራር በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በፋይናንስ እና በሌሎችም መስኮች የማይተካ ሚና እየተጫወተ ስለመሆኑ ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ታሳቢ በማድረግ መንግስት የዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ሀገራችን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ በ2028 1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት(GDP) ላይ ሊጨምር እንደሚችል ጂኤስኤምኤ(GSMA) የተባለ አለምአቀፍ ድርጅት ሪፖርት ላይ ተመላክቷል

በተጨማሪም ለመንግሥት ከ1 ሚሊየን በላይ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥርና ተጨማሪ 57 ቢሊየን ብር ከታክስ ገቢ እንደሚያስገኝም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ