+251118132191
contact@mint.gov.et
በዲጂታል ፐብሊክ መሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ተከናወነ
አውደ ጥናቱ በ ቶሊ ብሌር ኢንስቲትዩት አማካኝነት የተዘጋጀ ነው። በአውደ ጥናቱ ላይ አሁን የቶኒ ብሌየር ከፍተኛ አማካሪ እና የቀድሞ የህንድ ኤሌክትሮኒክ፣ ኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጅ እና ኢንተርፕሩነርሺፕ ሚኒስትር የነበሩት ሚ/ር ራጂቭ ቻንድራሴክሃር ህንድ የፐብሊክ መሰረተ ልማት ላይ በመመስረት ስላስመዘገበችው አስደናቂ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውጤት አስረድተዋል።
ሚ/ር ራጂቭ እሳቸው ሚንስትር በነበሩበት ወቅት የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ልማት ለማፋጠን ስትራቲጂያዊ እቅዶች እንዴት ይተገበሩ እንደነበረ እና የዲጂታል ፐብሊክ መሰረተ ልማቶች ይለሙ እንደነበር አብራርተዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ፣ ከዲጂታል መታወቂያ ጽ/ቤት፣ ከኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር፣ ከብሄራዊ ባንክ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢቲስዊች የተውጣጡ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
አውደጥናቱን በንግግር የከፈቱት ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በመተግበር በርካታ ውጤቶችን አስመዝግባለች ብለዋል።
አዲስ የተቀረጸው የዲጂታል መንግስት ስትራቴጂ ትኩረት ካረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ የዲጂታል ፐብሊክ መሰረተ ልማት እንደሆነ እና በተለይ የፋይዳ መታወቂያ መኖር በኢትዮጵያ የዲጂታል ፐብሊክ መሰረተ ልማትን በፍጥነት ለመተግበር መልካም እድል ይሰጣል ብለዋል።
የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ማለዳ ብስራት ቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሚሽንን እውን ለማድረግ ከመንግስት ጋር ተቀረርቦ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው፣ ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ መንግስት የሚያደርጋቸውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ተግባራት በመደገፍ ይሰራል ብለዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች